የኤርትራና የኢትዮጵያ ወታደሮች በትግራይ 182 ንፁሃን ገድለዋል – ዘ ቴሌግራፍ

0
566

በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህውሓት) እና ፌደራል መንግስት መካከል የተጀመረ ጦርነት በርካታ የትግራይ ሰላማዊ ዜጎች በጥይትና ከባድ መሳርያዎች ሰለባ እንዲሆኑ አደርጓል።

የካቲት 03 /2013 በማእከላዊ ትግራይ ተምቤን ዓብይ ዓዲ ከተማ ምንድነው የተፈፀመው?

ዘ ቴሌግራፍ የተባለ በለንደን መቀመጫው ያረገው ሚድያ በስፋት ጉዳዮን ሸፋን ሰጥቶ ተመልክቶታል፡፡

በማእከላዊ ትግራይ ዓብይ ዓዲ ተምቤን አከባቢ የሚኖሩ ዜጎች ደህና በሚባል ደረጃ የእለት እለት እንቅስቃሴ ላይ በነበሩበት ሰአት በድንገት የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ወታሮች ከተማዋን ከበቧት ይላል የአይን እማኞች ጠቅሶ የዘገበው ዘ ቴሌግራፍ።

የአይን እማኞች እንደ ተናገሩት ከሆነ ወታደሮቹ ቀጥታ ወደ ከተማ ከገቡ በኋላ ቤት ለቤት በመግባት ሰዎቹን መግደል ጀመሩ ፣ በዚህም በአጠቃላይ 182 ሰዎች ተገድለዋል።

ወጣት ተስፋየ ገ/መድህን የ26 እድሜ ያለው ሲሆን ከሌሎች ጓደኞቹ ጋር በመሆን በአከባቢው በሚገኘ ተራሮች በማምለጥ ሂወቱ ሊያተርፍ ችለዋል ። ተስፋየ በቦታው የነበረ ሁኔታ ሲያስታውስው እጅግ አሳዛኝ እንደ ነበር ለ ዘ ቴሌግራፍ ተናግሯል።

“የተበታተነ የሰዎች ሬሳ በቦታው ይታያል ፤ ሆኖም ወታደሮቹ ማንም ሰው ቢሆን ወደ ሬሳው ቀርቦ ማንሳት አይችልም ብለውን ነበር ፣ ግን ከትንሽ ጊዜያት በኋላ ሬሳው በመጥፎ ሽታ ስለ ረበሻቸው አፈር አስለበሱት” ሲል ተስፋየ ተናግረዋል፡፡

ከተምቤን ጭፍጨፋ አምልጣ ሂወትዋን ያተረፈችው የአምስት ዓመት እድሜ ያላት መርሃዊት ወልደገብርኤል አጎትዋ እስዋን ለማትረፍ ተተኩሰበት ህይወቱ ሊያጣ እንደቻለ ተናግራለች።

“ወታደረቹ መጡና አጎቴን ተኮሱበት፤ አባቴንም ተኮሱበት ከዛን አባቴ አምልጦ ሲሮጥ አጎቴን ግን መጀመርያ እግሩን መቱት- በኋላ ሆዱ ላይ ስለ ተኮሱበት ህይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ፤ እኔን ጉልበቴ ላይ ተኮሱበኝና መቱኝ” ስትል ከነበረችበት ዓይደር ሆሰፒታል አልጋ ሆና ነው በስልክ የተነገራቸው፡፡

መንግስት በትግራይ ክልል እየተደረገ ባለው ጦርነት ምክንያት በህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት እና የሰብአዊ መበት ጥሰቶች ቢክድም አሁን ግን በተለያዩ የአለም አቀፍ ተቋማት አምንስቲ ኢነተርናሽናል እና ኢንተርናሽናል ክራይሰስ ግሩፕ ጨምሮ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እያወጡት ባለ ሪፖርቶች በክልሉ ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እየተፈፀሙ ነው።

የኢትዮጵያ መንግስት መሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ወታደሮች በንፁሃን ዜጎች ላይ ጥቃት ከፈፀሙ ከተጠያቂነት አያመልጡም በማለት ለፓርላማ አባላት የተናገሩ ቢሆንም እስካሁን ግን የንፁሃን ሰዎች ሞትና እንግልት ግን አንደቀጠለ ነው።

ለዚም ማረጋገጫ ይሀ የካቲት 3 የተፈፀመው ኢ ሰብአዊ ድርጊትና በተለያዩ ጊዚያት የሚወጡ የቪድዮ ምስሎች እና የአለማቀፍ ሚድያ ዘገባዎች ያመለክታሉ፡፡

ከተምቤን ጭፍጨፋው አምልጦ ራሳቸውን ያዳኑ የአይን እማኞች ለ ዘ ቴሌግራፍ እንዳወሩት ከሆነ በብዛት የተገደሉት ገበሬዎች ናቸው።

በ ዓዲ አስሚዐን፤ በጋ ሸካ፤ ዓዲ ጭሎ፤ አምበርስዋ፤ ወትላቆ፤ ስምረት፤ ጉያ፤ ዘላክመ፤ ዓረና፤ ምፃወርቂ፤ ይቅየር እና ሽሉም እምኒ በተባሉ ገጠርማ ቦታዎች 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ከትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቐለ የሚገኙ ናቸው።

ዓዲ አስምዐን በተባለ ስፍራ በ ሃያዎቹ እድሜ እንደሆኑ የሚገመቱ አራት ወንደሟሞች ከ አንድ ቤት በወታደሮች ተገድለዋል። እነሱም ገ/መድህን፤ ክብሮም፤ ጉዕሻይ እና ተስፋማርያም አርአያ ይባላሉ ይላል ዘ ቴሌግራፍ ዘገባ።

ወንድሟሟቸቹ በአጨዳ ላይ እያሉ ነበር የኤርትራ አና የኢትዮጵያ ወተደሮች ያገኟቸው፡፡ ወታደረቹ ወጣቶችን በስፍራው አቅራብያ በመውሰድ ገድሎ ሬሳቸው በጉድጓድ አፋፍ ላይ ነበር የተጣሉት ይላል ዘገባው።

አባተቸው አቶ አርአያ ገ/ተክለ ከቦክር ልጃቸው መብራህቶም አርአያ ጋር በመሆን የቤተሰቦቻቸው ሬሳ ለመፈለግ ቢያንስ አምስት ቀናት ፈጅቶባቸዋል፡፡

“ልጆቼ ሲወስዷዋቸው እኔ በዚያ ሰአት ለቤት የሚሆን እቃ ልንገዛዛ ከቦክር ልጄ ጋር ገበያ ወጥተን ነበር ፤ ከገበያው ስመልስ የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ወታደሮች ከ ከሰፈራችን በቁጥር ብዛት ያላቸው ወጣቶች እንደወሰዱ ሰማሁኝ ። የእኔ ልጆችም ይኖርበታል ብየአሰብኩኝ” ይላሉ አቶ አርአያ።

አቶ አርአያ ልጆቻቸውን መለየት የቻሉ በለበሱት ልብስ ብቻ ነበር ፣ በተደጋጋሚ ሲጠይቁኝ ነበር እነዛ ሬሳዎች የልጆቼ መሆናቸው እርግጠኛ መሆኔ ነገርኳቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በትግራይ ክልል ውስጥ እየተደረገ ያለው ጦርነት በህግ ማሰከበር ስም የተጀመረ ቢሆንም በዜጎች ላይ ችግር እየፈጠረ መሆኑን የተለያዩ ሪፖርቹ ያሳያሉ።

የፌዴራል መንግሰት የትግራይ ክልል ጊዚያዊ መስተዳድርና የኤርትራ መንግሰት በትግራይ እየተፈፀመ ያለው ከፍተኛ ቀውስ መቼ ይቆማል ?,ቀጣይስ ወዴት ይሔዳል ለሚለው ጥያቄ ይህ ነው የሚባል የረባ መልስ አይሰጡም።

በትግራይ የንፁሃን ግድያ ከመብዛቱም በላይ በርካታ ዜጎች ለርሃብና ለችግር ተጋልጠዋል።

አውሎ ሚድያ ሚያዚያ 01 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ