ኡጋንዳ እና ግብፅ በድህንነት ጉዳይ የጋራ ስምምነት አድረጉ

0
425

ኡጋንዳ በወታደራዊ መረጃ ልውውጥ ዘርፍ ከግብፅ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችላትን ስምምነት መፈራረሟን ትናንት ረቡዕ መጋቢት 29 ቀን 2013 ዓ.ም አስታውቃለች፡፡ ስምምነቱ በሕዳሴ ግድብ ምክንያት በግብፅ እና ኢትዮጵያ መካከል “ውጥረት” በነገሰብት ወቅት የተደረገ መሆኑ፣ ጉዳዮን አነጋጋሪ አድረጎታል ሲል ሮይተርስ ዘግቦታል፡፡

ሰምምነቱን የተፈራረሙት በኡጋንዳ መከላከያ ኃይል የውትድርና መረጃ ኃላፊ እና የግብፅ መረጃ ዲፓርትመንት ተወካይ ናቸው፡፡

የካይሮን ልዑካን ቡድንን በመምራት ወደ ካምፓላ ያቀኑት የግብፅ ወታደራዊ መረጃ ሹም ሜ/ጀነራል ሳሜህ ሳበር በስምምነቱ ወቅት “ኡጋንዳ እና ግብፅ የናይልን ውሃ የደሚጋሩ እንደመሆናቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል ትብብር መኖሩ የግድ ነው፡፡ ምክንያቱም የአንዱ ፍላጎት በቀጥታም ሆነ በሌላ መንገድ ሌላኛው ላይ ተፅእኖ መፍጠሩ አይቀርምና” ማለተቻው ተገልጿል፡፡

የግብፁ ፕሬዝደንት አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ የግብጽ የውሃ ድርሻ ከቀነሰ “ምስራቅ አፍሪካ ለከፍተኛ ቀውስ ይዳረጋል” ካሉ ከሳምንት ያክል ቆይታ በኋላ ፣ የሕዳሴው ፕሮጀክት የግብፅን የውሃ መጠን የሚቀንስ ከሆነ “ውጤቱ ከባድ ይሆናል”ሲሉ በትናንትናው ዕለት በድጋሚ ዝተዋል፡፡

ፕሬዝደንቱ በድጋሚ ዛቻ አዘል ንግግር ያደረጉት በኪንሻሳ የተካሄደው የኢትዮጵያ ፣ የግብፅ እና የሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ሚኒስትሮች ስብሰባ ያለውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ነው፡፡

ኡጋንዳ ቀድም ሲል ግብፅ በላይኛቹ የተፋሰስ ሀገራት የሚከናወኑ ፕሮጅክቶችን ለመቆጣጠር የምትሄደውን “ያልተገባ ርቀትና ሙከራ” ስትቃወም እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

አሁን ላይ ሁለቱ ሀገራት “በወታደራዊ መረጃ” ልውውጥ መስክ አብረው ለመስራት የመስማማታቸው ዓላማ ምን እንደሆነ ግን በሮይተርስ ዘገባ ላይ የተገለጸ ነገር የለም፡፡

ነገር ግን ብህዳሴው ግድብ ዙራይ ጎረቤት ሃገር ሱዳንም ጭምር ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድቡን እንድታዘገየው ከፍተኛ ጥረት እያደረገች መሆኑን ሚዘነጋ አይደለም እንዲሁም ኢትዮጵና ሱዳን በድምበር ጉዳይ ላይ ሌላ ውጥረት ውስጥ እንዳሉም ሚታወስ ነው፡፡

አውሎ ሚድያ መጋቢት 30 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ