በደቡብ ክልል የአማሮ ወረዳ ነዋሪዎች «ኅልውናችን በአሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል» አሉ

0
386

በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ ነዋሪዎች «የታጠቁ» ቡድኖች በተለያዩ ቀናት በፈጸሙት ጥቃት 12 ሰዎች ተገድለው ከ11 ሺ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ዐስታወቁ።

በታጣቂዎቹ ጥቃት፣ ግድያና ዘረፋ ኅልውናችን በአሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶይቸ ቬለ (DW)ተናግረዋል።

ታጣቃዊዎቹ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ በልዩ ወረዳው የተለያዩ ቀበሌያት በመዘዋወር ባደረሷቸው ጥቃቶች ነዋሪዎች ከመገደላቸው በተጨማሪ የንብረት ውደሙ ተጠቅሷል። ነዋሪዎች የመኖርያ ቄዬአቸውን ለቀው ለመሰደድ መገደዳቸውን ጨምረው ገልፀዋል።

በተደጋጋሚ ከፍተኛ ጥቃት የሚፈፀምበት የአማሮ ወረዳ ኗሪዎቹ ስቃያቸውን የሚያቀልላቸው አካል አላገኙም። በተለይም ደግም በወንሰንና ሌሎች የልዩ ወረዳና የልዩ ዞን እንሁን የሚሉ ጥያቄዎች የፈጠሯቸው ታጣቂዎች በየጊዜው ግድያ የፈፀመቅ ንብረት እያወደሙ ይገኛሉ።

የአማሮ ወረዳና አካባቢ ችግሮችን በተመለከተ መፍፍተሔ የሚሆን ይህ ነው የተባለ ውሳኔ ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልልም ሆነ ከፌዴራል መንግስት ተሰጥቶ አያውቅም።

አውሎ ሚድያ መጋቢት 30 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ