በትግራይ ክልል ያለው ጦርነት በፍጥነት ላይቆም ይችላል ብሏል አለም አቀፉ የግጭት አጥኚ ደርጅት – ICG

0
392

የኢትዮጵያ መንግስት የህግ ማስከበር ዘመቻ የሚለው ጦርነት በቅርቡ ያበቃል ብሎ ማሰብ አስቸጋሪ መሆኑን በእንግሊዝኛ ምህጻሩ ICG በመባል የሚታወቀው እና ዋና መቀመጫውን ብራሰልስ ያደረገው በዓለማቀፍ ግጭቶች ዙርያ የሚሰራው ተቋም አስታወቀ።

የፌደራል መንግስት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህውሓት) በሰሜን እዝ ላይ ድንገተኛ ጥቃት ፈፅሞብኛል በማለት ያወጀው ጦርነት በድል ማጠናቀቁ ቢገልፅም እሁንም ቢሆን በገጠር አከባቢዎች የቀጠለ መሆኑን የተለያዩ አለማቀፍ ተቋማት እየገለፁ ይገኛሉ፡፡

እንዲሁም በገጠር አከባቢ ሚገኙ ዜጎች የጦርነቱ ሰላባ መሆናቸው እና የተለያዩ ጉዳት የደረሳቸው መሆኑ አይ ሲ ጂ ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የክራይስ ግሩፕ ተመራማሪ ዊልያም ዳቪሶን ከዶቼ ቬሌ ጋር ባደረጉት የስልክ ቆይታ እንዳሉት ከሆነ የህውሓት ኃይል የተጠናከረ መጥተዋል ከህዝቡም ድጋፍ እያገኘ ነው ይህም የሆነበት ምክንያት አብዛኛው የትግራይ ተወላጆች የሌላ ሃገር ጣልቃ ገብነትን አጥብቆ ሰለሚቃወሙ ነው፡፡ እንዲሁም ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ በሰላማዊ ሰዎች እየደረሰ ያለው ጥቃትና እንግልት ብዝዎች አስቆጥተዋል፡፡ ህዝቡ በነዚህ ምክንያቶች ድጋፍ እየሰጠ መሆኑ ነው ተማራማሪው የተናገሩት፡፡

ህውሓት ከውጭ መሳርያ ሊያቀርብለትና ሊያግዘው የሚችል አካል ባይኖረውም ህዝቡ ግን በደምብ እያገዘው ነው ሲሉ ተመራማሪው ተናግረዋል፡፡

ድርጅቱ መንግስት የኤርትራ ወታደር ከትግራይ ክልል እስወጣለሁ፤ የእርዳታ አቅርቦት በሁሉም ቦታዎች ተደራሽ አደርጋለሁ እንዲሁም በክልሉ እየተፈፀሙ ያሉት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በገለልተኛ አካል አጣራለሁ ማለቱ የሚደነቅ ሃሳብ ቢሆንም ይህ ሁሉ ግን ጦርነቱ ማቆሙን ይጠራጠራል፡፡

ተመራማሪው ግን የኤርትራ ወታደሮች ማስወጣቱ ጥሩ ሃሳብ ቢሆንም በትግራይ ክልል ያለው ጦርነት ለማቆም ግን ህውሓት እና ፌደራል መነግስት መደራደር ይጠበቀባችኋል ብለዋል፡፡

ሆኖም በትግራይ ክልል እየደረሰ ያለው የሴቶች መደፈር፤ የዜጎች ግፍና እንግልት ግን ፌደራል መንግስት በቻ ሳይሆን ህውሓትም ተጠያቂ ነው ብለዋል ተመራማሪው፡፡

ድርጀቱ በዘገባው ህውሓት ወደ ጦርነት የገባው ታንክ፤ ሮኬትና ላውንቸር ከባድ መሳርያዎች ታጥቆ ቢሆንም አሁን ግን በቀላል መሳርያዎች እየተዋጋ መሆኑን ፅፈዋል፡፡

በአመራር ደረጃም በጦርነቱ እየተሳተፉ ያሉት የቀድመው የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች አዛዥ ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ እና በቅርቡ ከመከላክያ ሰራዊት በጥሮታ የተገለሉት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ እንደሚገኙበትም ድርጅቱ ገልፀዋል፡፡

ተቋሙ ባለፈው ዓርብ በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ በሰጠው መግለጫው ዓለማቀፉ ማሕበረሰብ በቅድምያ ተኩስ ቆሞ በሁሉም የትግራይ አካባቢዎች እርዳታ እንዲደርስ ግፊት እንዲያደርጉ አሳስቧል።

አውሎ ሚድያ መጋቢት 30 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ