የኪንሻሳው ውይይት ያለስምምነት የጠናቀቀው በግብፅና በሱዳን ምክንያት ነው – ውጭ ጉዳይ

0
36

ግብጽ እና ሱዳን በሁለቱ ቀናት ውይይት ያልተነሱ ጉዳዮችን ካልተካተቱ በሚል ረቂቁን አልተቀበሉም፡፡ በመሆኑም ሁለቱ ሀገራት የአፍሪካ ህብረት ሂደትን የሚያሳንስ እና ጉዳዩን ከህብረቱ የሚያወጣ ስልት በመከተል እንዲሁም ምክክር የተደረገባቸውን ጉዳዮች የያዘ መግለጫ አንቀበልም በማለት ድርድሩ አዎንታዊ ውጤት እንዳይኖረው እንቅፋት ሆነዋልም ይላል የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ትላንት ባወጣው መግለጫ።

ይሁን እንጂ  የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ትላንት ባወጣው መግለጫ ካለምንም መፍትሄ ስብሰባው መጠናቀቁ ገልፆ ኢትዮጵያ በግብፅና በሱዳን የቀረቡት ድርድር ሂደት ሊያሳድግ ወይም ሊያፋጥን የሚችል ሁሉንም ፕሮፖሳል ውድቅ እድርገዋለች ማለታቸውም አይዘነጋም፡፡

በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ እየተከናወነ የሚገኘው የኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር ስለሚቀጥልበት ሁኔታ ለመመካከር በኪንሻሳ የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ሚኒስትሮች ስብሰባ ተካሂዷል፡፡

ስብሰባውን በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግስትመጋቢት 28 ቀን 2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ፣ ስብሰባው ያለፉትን ሂደቶች በመገምገም ድርድሩ የሚቀጥልበትን ሂደት ለመወሰን ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጿል።

የሁለቱ ሀገሮች አካሄድ የአፍሪካ ህብረትን ሚና የሚያሳንስ መሆኑን እና የኪንሻሳው ውይይት ያለስምምነት መጠናቀቁን ኢትዮጵያ ገልጻለች “ኢትዮጵያ በአባይ ውሃ የመጠቀም መብቷን የሚያቅብ ማናቸውም ዓይነት ስምምነት አትፈርምም” ሲል  የውጭ ጉዳይ ሚኒትር በግለጫ ያትታል፡፡

በስብሰባው ሶስቱም ታዛቢዎች (ደቡብ አፍሪካ፣ አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት) በታዛቢነት እንዲቀጥሉ ስምምነት የተደረሰ ሲሆን፣ ስለሚኖራቸው ሚና ሰፊ ውይይት ተካሂዷል። በዚህ ረገድ ሶስቱ ሀገራት የየራሳቸውን አቋም ያንጸባረቁ ሲሆን ፣ እንደ መግለጫው ከሆነ ኢትዮጵያ ሀገራቱ ሙሉ ባለቤት የሆኑበትን እና የአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍን የሚያስጠብቅ የድርድር ሂደት በመደገፍ ታዛቢዎች በሶስቱ ሀገራት በጋራ ስምምነት ሲጠየቁ ብቻ ሃሳብ ማቅረብ ለመፍቀድ ተስማምታለች፡፡ ግብጽ እና ሱዳን ታዛቢዎች ከአፍሪካ ህብረት እኩል ተሳትፎ የማድረግ ሚና ሊሰጣቸው ይገባል በሚል ያቀረቡት ሀሳብ ተቀባይነት እንዳላገኘ ተገልጿል፡፡ የሁለቱ ሀገሮች አካሄድ የአፍሪካ ህብረትን ሚና የሚያሳንስ መሆኑን ነው መግለጫው ያመለከተው።

በስብሰባው ማጠናቀቂያ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የአፍሪካ ኅብረት ሥራ አስፈጻሚ ምክርቤት ሊቀመንበር ፣ የቀረበውን ረቂቅ መግለጫ (communique) ኢትዮጵያ በመሰረቱ ለመቀበል መስማማቷን ገጻለች፡፡

ሁኖም  ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዓመት ሙሌት በመርሆዎች መግለጫ መሰረት በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ እንደሚከናወን መግለጫው ያትታል፡፡ በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ በግድቡ የሁለተኛ ዓመት ሙሌት ዙሪያ ተገቢውን መረጃ ለመቀያየር ዝግጁቷን በተደጋጋሚ ገልጻለች፡፡

ሁለቱ ሀገሮች ስምምነት ሳይደረስ ግድቡ መሞላት የለበትም በሚል የሚቀርብ አቋም የሕግ መሰረት የሌለው እንዲሁም የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሀብቷን የመጠቀም መብት የሚጋፋ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም፡፡ የግድቡ አሞላል እና ተያያዥኛ የውሃ እለቃቅ ስርዓት ላይ ለመስማማት ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ዝግጁ ብትሆንም ግብጽ እና ሱዳን በግድቡ ላይ የሚደረገው ድርድር እና

ውጤቱ የኢትዮጵያን የውሃ ድርሻ የሚገድብ እና አለን የሚሉትን የውሃ ክፍፍል የሚያጸና አስገዳጅ ስምምነት ካልተደረሰ የሚል ግትር አቋም ይዘዋል። ኢትዮጵያ ፍትሐዊ እና ምክንያታዊ የሆነ የአሁን እና የወደፊት በአባይ ውሃ የመጠቀም መብቷን የሚያቅብ ማናቸውም ዓይነት ስምምነት አትፈርምም።”

ኢትዮጵያ የድርድሩ ሒደት የሀገራቱን ሙሉ ባለቤትነት በሚያረጋግጥ እና የአፍሪካ ህብረትን የማስተባበር ሚና በተሟላ አኳኋን የሚያስጠብቅ የሶስትዮሽ ድርድር ለመከተል ዝግጁ መሆኗንም አስታቃለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሕብረት የወቅቱ ሊቀመንበር በሚያቀርቡት ጥሪ በቅርቡ ስብሰባው እንደሚቀጥል ትጠብቃለች በመግለጫው እንደተጠቀሰው።

ከሆነ የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ካለምንም መፍትሄ ስብሰባው መጠናቀቁ ገልፆ ኢትዮጵያ በግብፅና በሱዳን የቀረቡት ድርድር ሂደት ሊያሳድግ ወይም ሊያፋጥን የሚችል ሁሉንም ፕሮፖሳል ውድቅ እድርገዋለች ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል ግብፅ ይህን ወይይት ኢትዮጵያ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ከማካሄዷ በፊት ያለን የመጨረሻ ዕድል ስትል ጠርታው ነበር፡፡ እንዲሁም ሱዳንና ግብፅ ናይል ኤግልስ ዋን እና ናይል ኤግልስ ቱ የሚል ስያሚ የተሰጠው የሁለሽ የአየር ሃይል ልምምድ ማደርጋች ሚታወስ ሁኖ አላማውም በሁለቱም ሃገራት ድንበርና በህዳሴው ግድብ ምክንያት የሚመጣው ማነኛውም ሃይል የመመከት አላማ ያነገበ መሆኑን የሁለቱ ሃገራት ከፍተኛ የጦር አዛዦች መግለፃቸው ይታወሳል፡፡

አውሎ ሚድያ መጋቢት 29 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ