ከፍተኛ ትምህርት አግባብነት ጥራት ኤጄንሲ “ሲፈን ኮሌጅ” እነዲዘጋ ወሰነ

0
804

የእውቅና ፍቃድ ሳያገኝ በድህረ ምረቃ እና ቅድመ ምረቃ መርሃ ግብር ተማሪዎችን ሲያስተምር የተደረሰበት “ሲፈን ኮሌጅ” እንዲዘጋ ተማሪዎቹንም እንዲበትን መወሰኑን ሸገር ሬድዮ ዘግቧል።

ሲፈን ኮሌጅ አዲስ አበባ ጀሞ አካባቢ በከፈተው ካምፓስ በማስተር ኦፍ ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን በድህረ ምረቃ ደረጃ፣ በአካውንቲንግ ፋይናስን እና አድሚኒስትሬሽን በቅድመ ምረቃ ሲያስተምር ተደርሶበታል።

ይህ ኮሌጅ ከጥቂት ወራት በፊት በጉለሌ ክ/ከተማ በደንብ ማስከበር ፅ/ቤት(መንግስት ቢሮ) ውስጥ ተማሪዎችን ሲመዘግብ መገኘቱ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ፥ሲፈን ኮሌጅ እውቅና እንዲሰጠው ቢጠይቅም ዝቅተኛውን መስፈር ማሟላት ባለመቻሉ ማስተካከል ያለበትን ጉዳይ እንዲያስተካክልና በሶስት (3) ወር ውስጥ እንዲያሳውቅ ተነግሮት እንደነበር ገልጿል። ነገር ግን የኤጀንሲውን ምላሽ ችላ በማለት እውቅና ሳይኖረው ተማሪዎችን በተለያዩ ዲፓርትመንቶች መዝግቦ ሲያስተምር በድንገተኛ ክትትል ተደርሶበት እርምጃ እንደተወሰደበት አሳውቋል።

ኮሌጁ የከፈተውን ካምፓስ እንዲዘጋ፣እያሰተማራ ያላቸውን ተማሪዎች እንዲበትን፣አዲስ አበባ ውስጥ ለሚቀጥሉት 2 ተከታታይ ዓመት ምንም አይነት እውቅና እንዳይሰጠው ተወስኖበታል።

ኤጀንሲው ከሲፈን ኮሌጅ በተጨማሪ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ባሉ 5 ኮሌጆች (ፓራዳይዝ ቫሊ-ዲላ፣ ግሎባል ብሪጅ-ወ/ሶዶ)፣ ግሬት ላንድ- ነቀምቴ፣ ዘመን-ደሴ)፣ ራዳ -ደሴ) ላይ የእርምት እርምጃ መውሰዱን / ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ገልጿል፡፡

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመማር የሚመዘገቡ ተማሪዎች ተቋሙ የምዝገባ ፍቃድ እንዳለው ማረጋግጥ አለባቸው ሲል ከፍተኛ ትምህርት አግባብነት ጥራት ኤጄንሲ አሳስቧል።

አውሎ ሚድያ መጋቢት 29 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ