በትግራይ ከፍተኛ ሞት የሚያስከትል ርሃብ ሊከሰት አንድ ደረጃ ብቻ ነው የቀረው- የዓለም የሰላም ፋውንዴሽን

0
681

የዓለም የሰላም ፋውዴሽን (World Peace Foundation) በትግራይ ክልል እየተካሄደ ባለዉ ጦርነት ምክንያት በቀን ከ50-100 የሚሆኑ የክልሉ ኗሪዎች በቀን ምግብ ሳያገኙ ይዉላሉ በዚህም ምክንያት ተርበው ይሞታሉ በማለት ትላንት ባወጣው ጥናት አሳውቋል።

በአሜሪካዉ የሚገኘው የዓለም የሰላም ፋውንዴሽን የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የኤርትራ ወታደሮችና የአማራ ሚሊሻ በትግራይ ክልል በሰፊዉ የማስራብ እርምጃ እየወሰዱ ነዉ ብሏል፡፡

ይህ የማስራብ እርምጃ በቀን ከ50-100 የሚሆኑ ዜጎች ህይወታቸዉን እንዲያጡ ያደርጋል፡፡

ሪፖርቱ ያክላል መንግስት በክልሉ ዙርያ እየወጣ ያለዉን መረጃ የተጋነነ ነዉ ቢልም አለም አቀፍ ጋዜጠኞችና በጎ አድራጎት ድርጅቶች በሰፊ የክልሉ ቦታዎች በመሄድ አለመቻላቸዉ ህዝቡ ሆን ተብሎ እንዲራብና እንዲሞት እየተደረገ መሆኑን ድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡

በጥናቱ መሰረት 5.7 ሚልዮን ህዝብ ይኖርባታል የምትባለዉ ትግራይ በዚህ ሰአት 4.5 ሚልዮን የሚሆን ህዝቧ በጦርነቱ ምክንያት ህይወቱ አደጋ ላይ እንደሆነ የአሜሪካ መንግስት ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

የዓለም የሰላም ፋውዴሽን አካሄድኩት ባለዉ ጥናት መሰረት የትግራይ ህዝብ በ4ተኛ የርሃብ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ አንድ ማህበረሰብ ርሃብ አጋጥሞቷል የሚለዉ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ 5ት ደረጃዎች አሉ፡፡ ስለዚህ በትግራይ ከፍተኛ ርሃብ ተከስቷል ለማለትና የክልሉ ህዝብ ተርቧል ሊባል የቀረዉ ደረጃ አንድ ደረጃ ብቻ ነዉ፡፡ 5ተኛ ደረጃ ላይ ከደረሰ ብዙ ህይወት በረሀብ ይቀጠፋልም ነው ያለው ተቋሙ፡፡

ወደ ክልሉ የዘመተዉ ሀይል ሆን ብሎ የህዝቡ ንብረት በመዝረፍ ፣ እንዲሰረቅ በማድረግና ከማሳ የተሰበሰበዉን እህል በማበላሸትና በመድፋት ህዝቡ የሚበላዉንና የሚቀምሰዉን እንዲያጣ ተደርጓል ነው የሚለው ሪፖርቱ።

ፋብሪካዎችን በማዉደም በፋብሪካዎቹ ይሰራ የነበረዉን ቅጥር ሰራተኛ ካለ ደመወዝ እንዲቀር ተደርጓል ፤ ባንኮች በመዝረፍ ካዝናቸዉ ባዶ ቀርቷል፤ 400 ሺህ ኗሪ ብር እያለዉ በአገሎግሎት እጦት ሆዱ ተርቦ እንዲያድር ሆኗል ብሏል ፋውዴሽኑ።

አውሎ ሚድያ መጋቢት 29 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ