ሱዳን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ከአብዬ ይወጣልኝ አለች

0
382

ሱዳን በአብዬ ግዛት የሚገኘው የኢትዮጵያ ሰላም አስካባሪ ኃይል ከቦታው ለቆ ይወጣልኝ በማለት የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን (ተመድ) ጠይቃለች።

በኪንሻሳ የተካሄደው የግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ያለስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ ነው  ሱዳን ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰቸው ተብሏል።

የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር ከአብዬ ግዛት እንዲወጣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር እየተነጋገሩ መሆኑንም ሱዳን ገልጻለች። የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል በተመድ ስር በመሆን በሱዳንና በደቡብ ሱዳን መካከል በምትገኘውና ሁለቱ ሀገራት ይገባኛል ጥያቄ የሚያቀርቡባት አብዮ ግዛት በፈረንጆቹ በ2011 ጀምሮ ሰላም ለማስከበር ሰፍሮ ቆይቷል፡፡

አብዬ ግዛት በነዳጅ እና ሌሎች የተፈጥሮ ሀብቶች የበለጸገች ግዛት ናት። በዚህም ምክንያት ደቡብ ሱዳን ነጻነቷን እንደ በፈረንጆቹ 2011 ነጻነቷን መቀዳጀቷን ተከትሎ ነበር ሁለቱ ሀገራት ወደ ግጭት ያመሩት።

በሁለቱ ሀገራት መልካም ፈቃድ፣ ኢትዮጵያ በዚች ግዛት ሰላም እንዲሰፍን ከ4 ሺህ በላይ ጦር ወደ ሰፍራው አቅነቶ ሰላም በማስከበር ላይ ይገኛል።

ኢትዮጵያ ሱዳን እና ግብጽ በሱዳን በኪንሻሳ የተካሄደው የግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ያለስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ ሱዳን በአብዬ ግዛት ያለው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር እንዲወጣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ መሬም አልሳዲግ አልመሀዲ በኩል አስታውቃለች።

በአብዬ ግዛት ላይ በተሰማራው የኢትዮጵያ ሰራዊት ላይ እምነት የለንም ያሉት ሚኒስትሯ ጦሩ በፍጥነት አብዬን ለቆ እንዲወጣ እንፈልጋለንም ብለዋል።

እንደ ሚኒስትሯ ገለጻ ከሆነ ኢትዮጵያ በድርድሩ ላይ ግትር አቋም አሳይታለች፤ በኬንሻሳ የተካሄደው የሶሰትዮሽ ድርድር ያለስምምነት የተጠናቀቀው ኢትዮጵያ ስላልፈለገች ነው ብለዋል።

ሚኒስትሯ አክለውም ኢትዮጵያ በሱዳን ላይ ብዙ ፍላጎት አላት ፤ሱዳን ጥቅሟን ለማስከበር ብዙ አማራጮችን ትጠቀማለች ብለዋል።

ኢትዮጵያ ያለችበትን የውስጥ ችግር ሱዳን ተረድታ ለረጅም ጊዜ ታግሳለች፤በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ተቀብለናል ያሉት ሚኒስትሯ ከእንግዲህ ግን ይህ ያበቃል በቀጥታ ብሔራዊ ጥቅማችንን ማስከበር ላይ እናተኩራለን ሲሉ በኬንሻሳ ተናግረዋል።

ይህ እንዲህ እንዳለ ትላንት በህዳሴው ግድብ ዙርያ ኢትዮጵያ በውጭ ጉዳይ ሚኒሰትርዋ ባወጣች መግለጫ መሰረት  የኪንሻሳው ውይይት ያለስምምነት የተጠናቀቀው ብግብፅና በሱዳን መሆኑን ገልፃለች ሁኖም ሱዳን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪዎች ከአብዮ ይውጣልን ማለትዋ ተከትሎ እስካሁን በኢትዮጵያ በኩል ምንም አልተባለም፡፡

አውሎ ሚድያ መጋቢት 29 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ