የዐቃቤ ህግ በእነ ጃዋር መሀመድ ላይ በዝግ ችሎት ምስክር ላሰማ ጥያቄ ውድቅ ሆነ

0
120

የዐቃቤ ህግ በእነ ጃዋር መሀመድ ላይ በዝግ ችሎት ላሰማ ያለው የምስክር የአሰማም ሂደት ጥያቄ ውድቅ ሆነ፡፡

ዐቃቤ ህግ ባለፈው ቀጠሮው በምስክር ጥበቃ አዋጅ መሰረት ለምስክሮቼ ደህንነት ሲባል ከመጋረጃ በስተጀርባ እና በዝግ ችሎት ምስክሮቼን ላሰማ ሲል አቤቱታ አቅርቦ ነበር፡፡

ተከሳሾቹም የመከላከል መብታችንን የሚገድብ እና የዐቃቤ ህግ አቤቱታ ታማኝነት የለውም በማለት የዐቃቤ ህግ አቤቱታ ውድቅ እንዲደረግ ማመልከታቸው ይታወሳል።

በዚህ መሰረት የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የጸረ ሽብርና የህገ መንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ጥያቄውን መርምሮ ውድቅ አድርጎታል፡፡

በዚህም ዐቃቤ ሕግ ባለፈው ቀጠሮ በምስክር ጥበቃ አዋጅ 699/2003 አንቀጽ 4 /1 ሸ እና ቀ መሰረት ለ146 ምስክሮች ጥበቃ ተደርጓል ብሎ ከመጥቀስ በዘለለ ምስክሮች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት በማስረጃ ያላስደገፈ በመሆኑ በቂ ምክንያት ሆኖ አላገኘሁትም ሲል ፍርድ ቤቱ ምስክሮቹ በግልጽ ችሎት ምስክርነታቸውን እንዲሰጡ ብይን ሰጥቷል።

ይሁን እንጂ ተከሳሾቹ የምስክር ዝርዝር ይገለጽልን ብለው ያቀረቡት አቤቱታን በተመለከተ ግን ፍርድ ቤቱ የምስክር ዝርዝር ለምስክሮች ደህንነትና መብት ጥበቃ ሲባል የምስክሮች ማንነት እንዳይገለጽ ሲል ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል።

በዚህም መሰረት የምስክሮች ዝርዝር ሳይገለጽ ምስክርነታቸው በግልጽ ችሎት እንዲሰማ ሲል ፍርድ ቤቱ  ብይን ሰጥቷል።

በተጨማሪም ሁሉም ተከሳሾች የጠየቁት የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደርጎ የአቃቤ ህግ ምስክርን ለመስማት ለሚያዝያ 5 ቀን 2013 ተለዋጭ ቀን ቀጠሮ ተሰጥቷል ሲል ፋና ቲቪ ዘግቧታል፡፡

አውሎ ሚድያ መጋቢት 28 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ