አሜሪካ ሱዳን እና ኢትዮጵያ ውዝግባቸው እንዲያረግቡ ጠየቀች

0
224

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ብሊንከን ከሱዳን ጠ/ሚ አብደላ ሓምዶክ ጋር በስልክ በነበራቸው ቆይታ ሱዳን እና ኢትዮጵያ በደንበርና በህዳሴው ግድብ ዙርያ ያላቸው ውዝግብ እንዲያረግቡ ጠይቀዋል፡፡

የሁለቱም ሃገራት ውዝግብና መቃቃር ከትግራይ ክልል ደም አፋሳሽ ጦርነት ሊብስ እንደሚችል ስጋታቸው አስቀምጠዋል፡፡

አንቶንዮ ብሊንከን ከሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ ሓምዶክ ጋር በነበራቸው የስል ቆይታ ሱዳን እና ኢትዮጵያ ብአልፋሸቃ ድንበርየ ያለው አለመግባባት ሁለቱም ሃገራት በጠረቢዛ ዙርያ ችግራቸው መፍታት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

በመጋቢት ወር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ ከሱዳን ጋር ሁኖ ከሌሎች የጎረቤት ሃገራት ምንም አይነት ጠብ እንደማይፈልጉ ለተወካዮች ምክርቤት መግለፃቸው ይታወሳል፡፡

ከዚ ጋር በማቆራኘት አንቶኒዮ ብሊነከን በቅርብ ችግራቸው ለመፍታት እንዳሳዩት ፍላጎት አሁንም በዛው መቀጠል አለባቸው ገልፀዋል ሲሉ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስራቤት ቃል አቀባይ ኔድ ገልፀዋል፡፡

የአልፋሽቃ ለም የሆነ መሬት ለሁለቱም ሃገራት ለግጭትና ጭቅጭቅ መንስኢ ሁነዋል ያሉት የውጭ ጉዳይ ምኒስትሩ አልፋሽቃ በትግራይ ክልል በጦርነት ተሰዶ ወደ ሱዳን የገቡ ኢትዮጵያውያንም ማቆያ ስፍራ ሁነዋልም ብለዋል፡፡

ብሊንከን ከዚ በተጨማሪ ሱዳን እና ኢትዮጵያ በህዳሴው ግብ ዙርያ መስማማት እንዳለባቸው እስገንዝበዋል፡፡

አሁንም ቢሆን የህዳሴው ግድብ በሰወስቱ ሃገራት ያለው ውዝግብ እየጨመረ መሆኑ በሃገራቱ መሪዎች እየወጡ ያሉትን መግለጫዎች ያመለክታሉ ከዚ ጋር በመያያዝ ግብፅ በኪንሳሻ የተጀመረው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ውይይት ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት ከመደረጉ በፊት ስምምነት ላይ ለመድረስ የመጨረሻው እድል ሊሆን ይችላል ብላለች።

ግብፅ ይህን ያለቸው ግብፅ ፣ ኢትዮጵያና ሱዳን በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ እየተደረገ የሚገኘውን ውይይት አስመልክታ ባወጣችው መግለጫ ነው።

ዛሬ ሰኞ እንደሚጠናቀቅ በሚጠበቀው ውይይቱ 3ቱ ሃገራት በዕድሉ ተጠቅመው ከመጪው ክረምት በፊት ከአንዳች ስምምነት እንዲደርሱ ፍላጎታቸው መሆኑን የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አሳእቋል።

ሶስቱን ሃገራት የማደራደር ሃላፊነቱን የተረከቡት የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት እና የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ፍሌክስ ሺሴኬዲ «ሃገራቱ አንድ አልያም በርካታ የተስፋ በሮችን ይከፍቱ ዘንድ አዲስ ጅማሬ እንዲያሳዩ እጋብዛለሁ » ብለዋል።

በእሁዱ ውይይት ስለተነሱ ሀሳቦች ሆነ ስለተደረሰ ስምምነት የተባለ ምንም ነገር የለም።

የግብጹ ፕሬዚዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ ባለፈው ሳምንት የግብጽ የውሃ ድርሻ ከተነካ «በቀጣናው አለመረጋጋት ሊያስከትል ይችላል።» ብለው ነበር።

ምንም እንኳ ግብጽ እና ሱዳን ሁለተኛው ዙር የውኃ ሙሌት እንዲራዘም ቢፈልጉም ኢትዮጵያ ሁለተኛውን ዙር የግድቡን ውኃ ሙሌት የፊታችን የክረምት ወራት የመሙላት ዕቅድ እንዳላት ቀደም ብላ አስታውቃለች ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

ኢትዮጵያ ባሁን ስአት በተለያዩ ጉዳዮች ውጥረት ላይ እንዶሆንች የሃገሪትዋ ምሁራን ጨምሮ የመንግስታ አካላት ሳይቀር መግለፃቸው ይታወሳል፡፡

ይህ እንዲህ እንዳለ አሜሪካ በትግራይ ክልል የተደረግ ላለው ጦርነት ምክንያ በንፁሃን ዜጎች እየተፈፀመ ያለውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እና ግድያ መቆም እንዳለበት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶንዮ ብሊንከን በኩል መግለፀዋ ይታወሳል፡፡

አሁን ደሞ “አሜሪካ በትግራይ የተፈጸሙ ጭፍጨፋዎች ሪፖርቶችን እየመረመረች ነው” ሲሉ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ተናግረዋል ሲል ሮይተርስ በድረ ገፁ አስነብበዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በባለፈው ቅዳሜ የኤርትራ ወታደሮች ማሰወጣት ጀምሪያለሁ ማለቱ ተከትሎ የአሜሪካ መንግስት እንደሚደግፈውና በትግራይ ክልል ያለው ቀውስ ለመቀነስ የመጀመርው እርምጃ ነው ሲሉም ቃል አቀባዩ ገልፀዋል፡፡

አውሎ ሚድያ መጋቢት 28 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ