ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) አረፉ

0
251

ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) አረፉ፤ የቀብራቸው ስነ ስርዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ነገ ይፈፀማል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በልዩልዩ ኃላፊነት እና በመንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ የበላይ ጠባቂነት ያገለገሉት ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) አርፈዋል።

የብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ጸሎተ ፍትሐት ነገ መጋቢት 28 ጠዋት 4 ሰዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የሚደረግ ሲሆን የቀብር ስነ ስርዓተቸውም ከቅዳሴ በኋላ በዚሁ ቤተ ክርስትያን የሚፈጸም ይሆናል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ እና የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የበላይ ጠባቂ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከአባታቸው ባራምባራስ ተስፋ ተክሉ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ታህሣ ኃይሉ በ1930 ዓ.ም ግንቦት ወር በትግራይ ክልል ብዘት ወረዳ ነበር የተወለዱት።

ብፁዕነታቸው በተወለዱ በ83 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን ከቤተክርስቲያንቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አውሎ ሚድያ መጋቢት 28 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ