በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ11 ሺህ በላይ ሰዎች በ ኤች አይ ቪ ኤድስ እንደሚያዙ ተነገረ

0
263
Blood sample with sexually transmitted diseases: HIV, HBV, HCV, Syphilis

የፌደራል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ፅ/ቤት፤ በኢትዮጵያ በየአመቱ ከ11 ሺህ 715 በላይ ዜጎች በኤች አይ ቪ ቫይረስ እንደሚያዙ አስታውቋል፡፡

በአሁኑ በኢትዮጵያ በሁሉም የእድሜ ክልል ከ622 ሺህ በላይ ዜጎች ኤች አይ ቪ በደማቸው እንደሚገኝባቸውም ገልጿል፡፡

እንዲሁም ከ12 ሺህ 689 በላይ የሚሆኑት ሰዎች ደግሞ በኤድስና ተያያዥ በሽታዎች ህይዎታቸውን እንደሚያጡም ፅ/ቤቱ አስታውቋል፡፡

በሌላ በኩል ወደ ግማሽ  ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች የፀረ ኤች  አይ ቪ መድሃኒት  ህክምና  በመውሰድ ላይ እንደሚገኙም  ፅ/ቤቱ ጠቁሟል፡፡

በፈረንጆቹ በ2003 ገደማ የፀረ ኤች አይ ቪ ኤድስ ህክምና በሀገራችን መሰጠት ሲጀምር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው ይገኝ ነበር፡፡

የስርጭት ምጣኔውም በከተሞች 12 ነጥብ 6 በመቶ ሲሆን በገጠር ደግሞ 2 ነጥብ 6 ከመቶ እንደነበር መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ከአንድ አመት በኋላ በ2004 ደግሞ 105 ሺህ ሰዎች አዲስ በቫይረሱ ሲያዙ 90 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱና ባስከተላቸው ተያያዥ በሽታዎች ህይወታቸው ማለፉ ተገልጾ ነበር፡፡

ከ265 ሺህ በላይ ዜጎች ደግሞ የፀረ ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያ መድሃኒት ያስፈልጋቸው እንደነበር በወቅቱ የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል ሲል ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧታል፡፡

አውሎ ሚድያ መጋቢት 28 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ