በትግራይ ክልል የደም እጥረትም እንዳለ ተገለጸ

0
74
Human blood in storage

በትግራይ ክልል የደም ልገሳው አሁንም ከአዲስ አበባ እንደሚላክ እና  እጥረትም እንዳለ ተገለጸ፡፡

በአንጻራዊ ሁኔታ በመቀሌ ያለው የደም ባንክ ስራ ቢጀምርም አክሱም እና ሁመራ አሁንም ተረጋግተው ወደ ስራ መግባት እንዳልቻሉ ተነግሯል፡፡በበቂ ሁኔታ ደም መቅረብ ባለመቻሉ ከአዲስ አበባ በሽሬ በኩል እየተላከ መሆኑን የደም ባንክ ዋና ዳይሬክተር አቶ ያረጋል በንቲ  ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በፊት በነበረው አሰራር በደም አቅርቦት ቀዳሚ ከሆኑ ክልሎች መካከል መቀሌ አንዱ ነው፡፡ይሁን እንጅ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የደም አቅርቦቱ በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነሱ እና ሰራተኞች እንደልባቸው ተንቀሳቅሰው መስራት ባለመቻላቸው ሆስፒታሎች ከህሙማኑ ቤተሰብ ደም ለመቀበል እንደተገደዱ አቶ ያረጋል ገልጸዋል፡፡

የደም ልገሳ እና ማዳረስ ከለጋሾች ለተጠቃሚዎች በነጻ የሚደረግ አገልግሎት መሆኑን የጠቀሱት አቶ ያረጋል በችግር ወቅት መሰል አሰራሮች የተለመዱ ቢሆኑም በዚሁ እንዳይቀጥል ዘላቂ መፍትሄ ሊበጅ እንደሚገባ ለአሐዱ ተናግሯል፡፡

አውሎ ሚድያ መጋቢት 28 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ