በህዳሴው ግድብ ዙርያ የሦስትዮሽ ውይይት ያለአንዳች መፍትሔ መጠናቀቁ ተገለፀ

0
336
DCIM100MEDIADJI_0644.JPG

በኪንሻሳ የተካሄደው የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ውይይት ያለአንዳች አዲስ የመፍትሔ አቅጣጫ መጠናቀቁ ተገለፀ፡፡

የሦስትዮሽ ውይይት ትናንት ሰኞ የተጠናቀቀ ሲሆን በታዛቢነት የወቅቱ አፍሪካ ህብረት ሊቀ-መንብር የዲሞክራቲክ ሪፕብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት ፍሌክሲ ሼስኬዲ ተሰይመውበታል፡፡

ይህ የሦስቱን ሀገራት የውጭ ጉዳይና የውሃ ሚኒስትሮች ያሳተፈው ውይይት ከዚህ ቀደሙ የተለየ እልባት ይዞ እንዳልመጣ አህራም ኦንላይን ዘግቧል፡፡

የሰሞንኛውን ውይይት በተለመከተ የኮንጎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ እየተጠበቀ ቢሆንም ለግብፅ መንግስት የሚወግነው አህራም ኦንላይን ከምንጮቼ አገኘሁ ብሎ ባሰራጨው ዘገባው የትናንት ሰኞ የድርድር ውሎ አዲስ  ሀሳብ ይዞ አልመጣም፡፡

ከውይይቱ አስቀድሞ እሁድ ዕለት በነበረ የመክፈቻ መርሃ-ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት ፍሌክሲ ሼስኬዲ በመዲናቸው ኬንሻሳ የሚደረገው ውይይት ጥሩ ውጤት ይገኝበታል ብለው ተስፋ ሰንቀውበት ነበር፡፡

በሌላ በኩል ግብፅ ደግሞ ይህን ወይይት ኢትዮጵያ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ከማካሄዷ በፊት ያለን የመጨረሻ ዕድል ስትል ጠርታው ነበር፡፡

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአውሮፓ ህብረት፣ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በድርድሩ ይሳተፉ የሚለውን ሀሳብ ውድቅ ማድረጓ ይታወቃል፡፡

አሁን ደሞ  የግብፁ ዴሊ ኒውስ የተባለው የዜና አውታር እንደዘገበው ከሆነ የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ካለምንም መፍትሄ ስብሰባው መጠናቀቁ ገልፆ ኢትዮጵያ በግብፅና በሱዳን የቀረቡት ድርድር ሂደት ሊያሳድግ ወይም ሊያፋጥን የሚችል ሁሉንም ፕሮፖሳል ውድቅ እድርገዋለች ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሁኖም ኢትዮጵያ ከዚ በፊት በግብፅና ሱዳን ይቀርቡ የነበሩ ፕሮፖዛሎች የኢትዮጵያ ውሃ መብት አጠቃቀም ማይጠብቁ በመሆናቸው በተደጋጋሚ ውድቅ ማድረግዋ ስትገልፅ መቆየትዋ ይታወሳል፡፡

አውሎ ሚድያ መጋቢት 28 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ