ሰሜን ኮሪያ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት በሚደረገው የቶክዮ ኦሎምፒክ አልሳተፍም ብላለች

0
172

ሰሜን ኮሪያ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት በሚደረገው የቶክዮ ኦሎምፒክ  የማልሳተፈውም ‹ስፖርተኞቼ በኮቪድ ይለከፉብኛል በማለት ራስዋን ከውድድር አግልላለች፡፡

ሰሜን ኮሪያ ታሪካዊ የተባለውን ውይይት ካደረገች በኋላ በ2018 በተዘጋጀው የክረምት ኦሊምፒክ ላይ 22 አትሌቶቿን ወደ ደቡብ ኮሪያ መላኳ ይታወሳል፡፡

የአሁኑ የሰሜን ኮሪያ ውሳኔ ታዲያ ደቡብ ኮሪያ ከዘወትር ባላንጣዋ ጋር ለመወያየት የሰነቀችውን ተስፋ የሚያጨልም ነው ተብሏል፡፡

የኪም ጆንግ ኡን አስተዳደር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በሀገሪቱ እንደሌለ በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል፡፡

የጤና ባለሙያዎች በአንጻሩ በሀገሪቱ ኮሮናቫይረስ አልተከሰተም የሚለው ነገር የማይሆን ነው  ብለዋል፡፡

አውሎ ሚድያ መጋቢት 28 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ