ኤርትራ ወደ አዲስ አበባ እና ዱባይ ከፌል በረራ እንደምትጀምር አስታወቀች

0
337

የኤርትራ ትራነስፖርት እና ኮምኒኬሽን  ሚኔስተር ከአስመራ ወደ አዲስ አበባ እና ዱባይ ከሚቀጥለው ሳምንት  ጀምሮ የንግድ በረራ እንደሚጀምር እስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ባወጣው መረጃ መሰረት በኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ምክንያት ወደ አገሯ እና ከአስመራ ወደ ሌሎች አገራት ይደረጉ የነበሩ በረራዎችን አግዳ ነበር።

በዚህም ከአስመራ ወደ አዲስ አበባም ሆነ ከአዲስ አበባ ወደ አስመራ የሚደረጉ በረራዎች አልነበሩም፡፡

ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በሳምንት ሁለት ቀናት ወደ አዲስ አበባ እና ወደ ዱባይ በረራዎች ይደረጋሉም ነው ያለው ሚኒስቴሩ በመግለጫው።

ይህም ተግባራዊ ለማደረግ ከፍተኛ የሆነ የኮረና ጥንቃቄ በማድረግና የወጡ መመሪያዎችን ተግባራዊ በማድረግ የንግድ በረራው ይደረጋል ሲል የማስታወቅያ ሚኒሰትሩ የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገፃቸው አስታውቀዋል፡፡

አውሎ ሚድያ መጋቢት 27 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ