አለማቀፍ የምግብ ፕሮግራም በጦርነት ለተጎዱ ዜጎች የእርዳታ ጥሪ አቅርቧል

0
204

አለማቀፍ የምግብ ፕሮግራም በትግራይ ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚሰራው ስራ የዘ ዊኬንድን በጎ ተግባር ሌሎችም እንዲቀላቀሉ  ጥሪ እቀረበ፡፡

በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህውሓት) እና ፌድራል መንግስት መካከል በተጀመረ ጦርነት ምክንያት ገበሬዋች ምርታቸው ሳይሰበስቡ መቅረታቸው ብዙ ችግርና መዘዝ ይዞባው ከመምጣቱ በተጨማሪም ቡዝዎች ከስራ ተፈናቅሎ ራሳቸውን ማሰተዳደር አቅቶቸው የእርዳታ ጠባቂ እንዲሆኑ ተገድዋል፡፡

በተጨማሪም ጦርነቱ ለንሮ ዉድነት ጭማሬ ምክንያት ሁኖ ብዝዎች ችግር ላይ መውደቃቸው የአለማቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋማት እንዲሁም የአለማቀፍ የምግብ ፕሮግራም ሪፖርቶችን ያመልክታሉ፡፡

ይህ እንዲ እንዳለ የአለማቀፍ የምግብ ፕሮግራም በትግራይ ክልል ውስጥ ሚገኙ የጦርነቱ ሰለባ ለሆኑ 1.4 ሚሊዮን ሰዎች ድጋፍ ለማድረግ እቅድ ማውጣቱ ገልፀዋል፡፡

ዓለም አቀፉ ዝነኛ አርቲስት ዘዊኬንድ ለትግራይ ድጋፍ የሚሆን 1 ሚሊዮን ዶላር ማበርከቱ ይታወሳል።

ድምጻዊው በይፋዊ የትዊተር ገፁ ላይ ባሰፈረው መልዕክት “በኢትዮጵያ ከጨቅላ ሕጻናት እስከ አዛውንቶች በጭካኔ ሲገደሉ እና ከፍርሃት የተነሳ ቤታቸውን ጥለው ሲፈናቀሉ ስሰማ ልቤ ይሰበራል” ብሏል።

ድምጻዊው አክሎም ለእነዚህ ዜጎች የዓለም ምግብ ፕሮግራም 2 ሚሊዮን ምግብ ማቅረብ የሚያስችለው የ1 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል።

የአለማቀፍ የምግብ ፕሮግራም ፕሬዜዳንት እና ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ባሮን ሴጋር ዘ ዊኬንድ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ለሚሰራው ስራ የአንድ ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ስላደረገ ምስጋና አቅርበውለታል።

ዘ ዊኬንድ የአንድ ሚሊዮን ድጋፍ ከማድረግ ባለፈም በይፋዊ የትስስር ገፆቹ ላይ ሌሎችም ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡

አውሎ ሚድያ መጋቢት 27 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ