በድርቅ ምክንያት ለችግር ለተዳረጉ ዜጎች ለመድረስ 65.5 ሚሊየን ዶላር ያስፈልጋል ተባለ

0
108

በምስራቅ ኢትዮጵያ በድርቅ ምክንያት ለችግር ለተዳረጉ ዜጎች ለመድረስ 65.5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚያስፈልገው በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ (ዩ.ኤን.ኦቻ) አስታወቀ።

በክልሉ በድርቅ ምክንያት ለችግር ለተጋለጡ ወደ 2.1 ሚሊየን ገደማ የሚጠጉ ሰዎች የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ አስቸኳይ ድጋፍ ያስፈልጋል ብላል።

ግጭቶች ፣ ድርቅ እና በየወቅቱ የሚደርሱ የጎርፍ አደጋዎች የሶማሌ ክልልን ጨምሮ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች የተለያዩ ሰብዓዊ ቀውሶችን ሲያስከትል መቆየቱንና የሰብአዊ ድጋፍ የሚስፈልጋቸው ሰዎች እንዲያሻቅብ ማድረጉን ድርጅቱ አስታውሷል።

ማስተባበሪያው ይህን ያሳወቀው ትላንት ባወጣው ሳምንታዊ መግለጫ ነው።

ዩ.ኤን.ኦቻ ባህላዊ የውሃ ምንጮች መድረቅ እና ከጉድጓድ ውሃ የሚወጡ የውሃ አቅርቦቶች ውስንነት ክፍተኛ ችግር እያስከተለ መሆኑን በመግለጽ ፤ በክልሉ በአፋጣኝ የዉሃ ማጓጓዣ ተሸከርካሪዎች አቅርቦት እንደሚያስፈልግ አስታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪ በኢትዮጵያ ያለው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭት ሰብዓዊ ድጋፍ የሚስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር እንዲጨምር ምክንያት መሆኑን ዩ.ኤን.ኦቻ በመግለጫው አስታውቋል።

አውሎ ሚድያ መጋቢት 27 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ