በሚያዚያ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርችሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

0
179

በሚያዚያ ወር ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር የሌሎች የነዳጅ ምርቶች የችርችሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት መስከረም 23 ቀን 2001 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ በየወሩ እንዲከለስ መመሪያ መስጠቱ ይታወቃል።

በዚሁ መሰረት የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከመጋቢት 26 እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ተግባራዊ የሚሆን የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጪ የሌሎች የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል።

ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ መሰረት በሚያዚያ ወር የአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ በሊትር 43 ብር ከ70 ሳንቲም እንዲሸጥ የተወሰነ ሲሆን በመጋቢት ወር ሲሸጥበት ከነበረበት ዋጋ የ5 ብር ከ5 ሳንቲም ጭማሪ እንዳለው አስታውቋል።

የዓለም የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ በየወሩ እየጨመረ እንደሚገኝና የኢትዮጵያ የነዳጅ የችርችሮ መሸጫ ዋጋ በወቅታዊ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ስሌት መሰረት ተግባራዊ ቢሆን አሁን በተግባር እንዲሸጥበት ከተወሰነው የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ አንጻር የተለየ ይዘት ሊኖረው እንደሚችል ገልጿል።

ይሁንና መንግስት የኢትዮጵያን ወቅታዊ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ነባራዊ ሁኔታ በማስገባት በሚያዚያ ወር ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጪ ሌሎች የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑን አመልክቷል።

በዓለም ገበያ ላይ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊደርግ እንደሚችልም ሚኒስቴሩ መግለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አውሎ ሚድያ መጋቢት 27 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ