ከእንግሊዝ በጠርሙስ ውስጥ የተላለፈ መልእክት ከ8 ወር በኃላ ኖርወይ ገባ

0
114

በኖርወይ እናት እና ልጅ በበህር ዳርቻ ላይ ሲራመዱ በስምንት ወራት ውስጥ ከ1000 ኪሎሜትር ርቀት በላይ ተጉዞ የደረስ የጥርሙስ መልእክት አገኙ፡፡

የ36 አመትዋ አይዳ ሆድኔቦ እንዳለችው ከሆነ ከ7 ዓመት ወንድ ልጅዋ ጋር ኖርወይ የሚገኝ እንድ ጆምፍላንድላንድ ደሴት ባህር ዳርቻ ላይ እየተጓዘች እያለ በእጅ የተፃፈ ማስታወሻ የያዘ የመስተዋት ጠርሙስ አገኙ፡፡

ፅህፉ እንደሚመለክተው ከሆነ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በሐምሌ ወር 2020 ሊሊ ካርተር በተባለች የ 10 ዓመት ልጃገረደች የተፃፈ ሲሆን ጠርሙሱ ካለበት 1033 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በእንግሊዝ ቻፕል ሴንት ሊዮናርስ ውስጥ ከሚገኘው የባህር ዳርቻ ወደ ባህር ለመወርወር ማቀድዋንም በድብዳቤው ገልፃለች፡፡

ድብዳቤው ጠርሙሱ ያገኘው ማነኛው ሰው በኦን ላይን እንዲፖስተው ትእዛዝ ይሰጣል ካርተር ካነበበችው ቡኃላ የጠርሙሱ ፎቶና ደብዳቤው በፌስቡክ ላይ ለቀቀችው፡፡

ሃራልድ ክርስትያኖች በፌስቡክ የተለቀቀውን የጥርሙሱ ፎቶ እና ደብዳቤ ካዩ ብኃላ የሆርኔቦ ፎቶግራፎችን በመልቀቅ እንዲሁም ለሎንግ ኢቶን ነዋሪዎች የፌስቡክ ገፃቸው ላይ በመቀላቀል የተወሰነ የምርመራ ስራዎችን ለመስራት ወሰኑ፤

በብድኑ የተለቀቀ የጠርሙሱ ፎቶ እና ደብዳቤ የ38 አመትዋ የሆነችው ክሌር ጴንቶኬስት የካርተር እናት ፎቶዎችን አየቻቸው፡፡

እናታቸው እንዳለችው “ሊሊ እና ክሎ የ11ዓመት ታላቅ እህቷ መልዕክቶች ወደ ባህር ውስጥ ላኩ፤ ግን እስካሁን ጠርሙሱ ያገኘ አልነበረም”፡፡ ክዳኑ መቆየቱና ወደ ውስጥ ውሃ ገብቶ አለመስመጡ ራሱ በጣም ሚያስገርም ነው ስትል ገልፃለች፡፡

አውሎ ሚድያ መጋቢት 25 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ