በጅሌ ጥሙጋ የሰዓት እላፊ ገደብ ታወጀ

0
320

የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት፥ የአካባቢውን ሰላም የበለጠ ለማረጋገጥ እንዲቻል በወረዳ ደረጃ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙን አሳውቋል።

ኮማንድ ፖስቱ የሰው እና የባጃጅ እንቅስቃሴ የምሽት የሰአት አለፊ ገደብ አስቀምጧል።

በዚህም መሰረት ባጃጅ እስከ ምሽቱ 2 ሰአት ሲሆን ሰዎች ደግሞ እስከ ምሽቱ 3 ሰአት ብቻ መንቀሳቀስ የሚችኑ መሆኑን ኮማንድ ፖስቱ አስታውቋል።

ከተጠቀሰው ሰአት ውጭ የሚንቀሳቀስ ሰውም ሆነ ባጃጅ ካለ የህግ እርምጃ እደሚወሰድበት የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ ቤት አሳስቧል።

በአማራ ክልል ኦሮሚያ ልዩ ዞን ጅሌ ጥሙጋ ባለፈው ሳምንት የተከሰተው አለመረጋጋት አሁንም አልፎ አልፎ የሚታይ በመሆኑ የሰዓት እላፊ ገደብ ለመጣል ምክንያት ሆኗል።

አውሎ ሚድያ መጋቢት 25 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOAድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ