በትግራይ ክልል 1 ሺህ 900 ሰላማዊ ሰዎች በጅምላ ጭፍጨፋ ተገድለዋል – ዘ ጋርዲያን

0
681

በትግራዩ ግጭት 1 ሺህ 900 ሰላማዊ ሰዎች በጅምላ ጭፍጨፋ እንደተገደሉ አንድ የቤልጂዬም ዩኒቨርስቲ አጥኝዎች ቡድን ማረጋገጡን ዘ ጋርዲያን አስነብቧል፡፡

ዩንቨርስቲው በትግራይ ክልልና በፌደራል መንግስት መካከል ጦርነት ከጀመረ ጀምሮ ጥናቱ ማድረግ እንደጀመረ ነው የተዘገበው። በ150 የተለያዩ ጭፍጨፋዎች ጨቅላ ሕጻናትን እና አረጋዊያንን ጨምሮ የሟቾችን ማንነት በቃለ ምልልሶች እና ከምስክሮች ጋር በተደረጉ የስልክ ግንኙነቶች ማረጋገጡን ቡድኑ ለዘጋርዲያን አረጋግጧል።

ወታደሮች፣ ሚሊሻዎች እና አማጺዎች በግድያው ተሳትፈዋል የተባለ ሲሆን በጦርነቱ ወቅት የንፁሃን ዜጎች ጭፍጨፋ ምንም እንኳን ብዙ የመንግስትና የአለማቀፍ ተቋማት ሪፖርት ቢያደርጉም ጠቅላይ ሚኒስተር ዐብይ አሕመድ ግን ሪፖርቶቹ የተጋኑና የተፈበረኩ ናቸው በማለታቸው የሚታወስ ነው።

የፌደራል መንግስት በሰሜን እዝ ላይ ድንገተኛ ጥቃት ከህዝባዊ ወያን ሓርነት ትግራይ (ህውሓት) በኩል ተፈፅሟል በማለት የተጀመረው ጦርነት ተጠናቋል የተባለ ቢሆንም እስካሁን ግን ጦርነቱ መቀጠሉ የተለያዩ ሪፖርቶችና የዓለማቀፍ ሚደያዎች ዘገባ ያመላክታሉ፡፡

የጥናቱ ቡድን እንደዘረዘረው ከሆነ ቢያንስ አምስት ሰዎች የሞቱባቸው ክስተቶች ተብለው የተገለጹ የተለያዩ ጥቃቶች ባለፈው ወር ውስጥ ተከስተዋል ። በተጨማሪም በምእራብ ትግራይ፤ በስተምስራቅ ትግራይ አካባቢዎች ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ እና ስትራቴጅካዊ ጠቀሜታ ባላት ሁመራ ከተማ ውስጥ በተከታታይ ከሶስት ቀናት በላይ በግምት 250 የሚደርሱ ሰላማዊ ሰዎችን እንደተገደሉ የአካባበዊ ነዋሪች ገልፀዋል ሲል የጥናት ቡድኑ ሪፖርቱን አውጥቶታል በማለት ዘጋርዲያን አስነብቧል፡፡

የጥናት ባለሞያዎች እንዳሉት ከሆን ከተለያዩ የትግራይ ክልል የተጎዱ ዜጎች 3 በመቶዎቹ በአየር ድብደባ ወይም በመድፍ የተገዱ ናቸው፡፡ አብዛኞቹ ተጎጂዎች ቤት ለቤት ፍተሻ የሞቱ ናቸው። በዋናኘት በአክሱምና በማይካድራ ነውሲሉ አጥኞዎች ይገልፃሉ፡፡

ይህም የተፈፀመ ያለው በዋነኝነት በኤርትራ ወታደሮች ጨምሮ የፌዴራል ወታደሮች ፣ የአማራና የህወሓት ሀይሎች መሆኑን የአለማቀፍ የስብአዊ መብት ጥሰቶች ሪፖርት ያመለክታሉ፡፡

በሌላ በኩል በትግራይ ክልል ቀውስ ከቀጠለ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በሌሎች የግጭቱ ተሳታፊ አካላት ላይ ማዕቀብ ሊጣል ይገባል ሲሉ ሁለት የአሜሪካ ኮንግሬስ ውጭ ጉዳይ ኮሚቴ አባላት ባሰራጩት ደብዳቤ ጥሪ አድርገዋል፡፡

የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ግጭቱን ለማስቆም ሁሉንም አማራጮች እንዲጠቀም ሁለቱ ተወካዮች አሳስበዋል፡፡

ደብዳቤውን ለአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እና ለግምጃ ቤቱ የጻፉት፣ የምክር ቤቱ ውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ሊቀመንበር ዲሞክራቱ ግሪጎሪ ሚክስ እና ሌላ የሪፐብሊካን ፓርቲ ተወካይ ናቸው፡፡

አውሎ ሚድያ መጋቢት 25 ዜና / 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ