የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ ግዛት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በፍጥነት እንዲወጡ የጂ 7 ሀገራት ጠይቀዋል

0
1120

የካናዳ ፣ ፈረንሳይ ፣ ጀርመን ፣ ጣልያን ፣ ጃፓን ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ዩኤስኤ የሚገኙበት የቡድን 7 ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ የትግራይን ወቅታዊ ጉዳይ በተመለከተ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡

በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርስ ያለውን “ግድያ ፣ ጾታዊ ጥቃቶችን ፣ ያለ ልዩነት የሚፈጸም ከባድ ድብደባ እና በትግራይ ነዋሪዎች እና የኤርትራ ስደተኞች ላይ የሚፈጸመውን አስገዳጅ መፈናቀል” እንደሚያወግዙ ይገልጻል፡፡ ሁሉም ወገኖች የዜጎችን ደህንነት ማረጋገጥ ፤ የሰብዓዊ መብቶችን እና ዓለም አቀፍ ህጎችን ማክበር እንዳለባቸውም በመግለጫው ተጠቅሰዋል፡፡

በግጭቱ ውስጥ ያሉ አካላት “ያልተገደበ ሰብዓዊ አቅርቦትን እንዲያቀርቡ እንጠይቃለን” ያሉት የቡድን 7 ሀገራት “በማዕከላዊ እና በምስራቅ ትግራይ ሰፊ አካባቢዎች ሁኔታዎች እየተባባሱ መሆናቸው እና የከፋ የምግብ ዋስትና ችግር መኖሩ ያሳስበናል” ብለዋል፡፡

እንዲሁም በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የኤርትራ ኃይሎች ከትግራይ ይወጣሉ በሚል ያወጡትን መግለጫ በደስታ እንደሚቀበሉም መግለጫው ጠቁሟል፡፡ ይህ ሂደት በፍጥነት ፣ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፈጸም እንዳለበትም ነው የተገለጸው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ ለተወካዮች ምክርቤት የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ክልል በሰብአዊ መብት ጥስት ካደረጉ በራሳቸው መንግስት ተጠያቂ እንደሚሆኑ ገልፀው ነበር፡፡

ሁኖም የኤርትራ መንግስት በትግራይ ክልል የደረሱ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሙሽን ባወጣው ሪፖረት በአክሱም ከተማና በሌሎች አከባቢ የተደረገው ጭፍጨፋ ሃሰት ነው ሲል ማጣጣሉን ሚዘነጋ አይደለም፡፡

አውሎ ሚድያ መጋቢት 24/ 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ