በህዳሴ ግድቡ እና የግብፅና የሱዳን ወታደራዊ ጥምረት

0
129
DCIM100MEDIADJI_0644.JPG

ሱዳን በህዳሴ ግድብ ዙርያ ኢትዮጵያ ስምምነት ሳትደርስና የማሰሪያ ውል ሳይፈፀም ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት ማከናወን የለባትም የሚል አቋም አላት። ይህንንም ሀሳብ ግብፅ ሙሉ በሙሉ ቀድሞ ያነሳችው ነው። ይህንን ተገባራዊ ለማድረግ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንድታደርግ በግልፅ ጥሪ አቅርባለች ሲል ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል።

ከሰሞኑ በአለቃ ግርማና መንፈስ ብቅ ያሉት የአሜሪካ ልዩ መልእክተኛ ዶናልድ ቡዝ እና በሱዳን የአውሮፓ ህብረት ተወካይ ሮበርት ቫን ዴን ዶል ከሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ኃላፊ ላሌተናል ጀኔራል አብዱፈታህ አል ቡርሃን ጋር በህዳሴው ግድብ እና ድንበር ውዝግብ በተመለከተ ሰኞ መጋቢት 19 መወያየታቸው ይታወሳል፡፡

ይህ እንዲ እንዳለ ከትላንት ወድያ ማክሰኞ በስዊዝ ቦይ ጉብኝት ያደረጉት የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ በስፍራው ተገኝተው ለነበሩ ብዙሃን መገናኛዎች ዛቻ አከል ንግግር አድርገዋል።

“ከግብጽ ውሃ ማንም አንዲትንም ጠብታ ሊነካ አይችልም” ሲሉ የተናገሩት ሲሲ “ይህ ከሆነ ግን ማንም ሊያስበው የማይችል አለመረጋጋት በቀጣናው (ምስራቅ አፍሪካ) ይፈጠራል” ሲሉ ማሳሰባቸው የሚታወስ ነው፡፡

ይህንን ተከትሎም አራት የአረብ ሀገራት ግብፅን ደግፈው መግለጫ ማውጣታቸውና ኢትዮጵያላይ ዲፕሎማሲያዊ ጫና ማሳደር ጀምረዋል።

እንዲሁም የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒሰተር ማሬም ዐል ማህዲ ከልዩ የአሜሪካ መልእክተኛ ዶናልድ ቡዝ ጋር በህዳሴው ግደብና ሁለትየሽ ግንኝነት ተወያይተዋል፡፡

የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከውይይተ በኋላ በሰጡት በግለጫ ኢትዮጵያ ግድቡን የሚመለከታቸው አካላት ሳይስማሙ መሙላት እንደሌለባት በእዚህም አሜሪካ መሰረታዊ ድርድር እንድታደረግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሱዳንና ግብፅ አስቀድመው የህዳሴ ግድቡ ድርድር ከአፍሪካ ህብርተ ማዕቀፍ በተጨማሪ በአሜሪካ በአውሮፓ ህብርትና በተመድ አደራደሪነት መካሔድ አለበት በማለት ያቀረቡትን ሀሳብ ኢትዮጵያ አልተቀበለችውም ነበር።

ሱዳን በውጭ ጉዳይ ሚኒቴርዋ እንዲህ ብትለም የኢትዮጵያ አቋም እስካሁን ዝንፍ አላለም ። ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ህብረት ውጪ ማንም አዳራዳሪ እንደማትፈልግ በተደጋጋሚ መግለጿን ቀጥላለች።

ላለፉት አስር ዓመታት ኢትዮጵያ ፣ ግብፅ እና ሱዳን በሕዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ ሲደራደሩ ቢቆዩም ስምምነት ላይ መድረስ ግን አልቻሉም፡፡

ኢትዮጵያ የግድቡን ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በቀጣዩ ክረምት እንደምታከናውን አስታውቃለች፡፡ ለዚህም የደን ምንጣሮ ለማካሔድ ዝግጅት ተጠናቋል፡፡

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምስራቅ አካባቢ ቃል አቀባይ ሳሙኤል ዋርበርግ ባወጡት መግለጫ “በሕዳሴ ግድብ ልዩነት ውስጥ ያሉ ወገኖች በድርድር መፍትሄ ላይ እንዲደርሱ እንጠይቃለን” ብለዋል፡፡

የዓባይ ወንዝ ለግብፅ ፣ ለሱዳንና ለኢትዮጵያ ህዝቦች ያለውን ጠቀሜታ ተገንዝበን ለሕዳሴ ግድብ ችግር ሰላማዊ መፍትሄ ለማምጣት ማንኛውንም እርዳታ ለመስጠት ዝግጁ ነን ሲሉም ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።

ነገር ግን ኢትዮጵያ በበኩሏ ሁለተኛውን ዙር የሕዳሴ ግድብ ሙሌት በተያዘው ጊዜ እንደምናከናውን ለአሜሪካ ልዑክ ገልፃለች በማለት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል።

ዛሬ የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ባለስልጣናት የግብፅ ፣ የኢትዮጵያ እና የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በመጪው ቅዳሜ በኪንሻሳ ተገናኝተው በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ ብለዋል።

የኮንጎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ለሦስት ቀናት የሚካሄደውን ስብሰባ ባለፈው ወር የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበርነትን የተረከቡት ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ቺሲኬዲ ይመሩታል፡፡

የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ በውይይቱ ላይ እንደሚገኙም ተገልጿል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከአራት ወራት በፊት የጋራ ወታደራዊ የአየር ሀይል ልምምዶች ማድረግ የጀመሩት የሱዳን እና ግብፅ ጦር ዛሬ ልዩ ኦፕሬሽን ክፍሎችን በማሳተፍ አዲስ የጋራ የአየር ልምዶች እያካሔዱ ነው።

ህዳር 6/2013 የሁለቱም ሃገራት የአየር ሀይል አባላት ከካርቱም በስተ ሰሜን በሱዳን ማራዊ ወታደራዊ አየር ማረፍያ ውስጥ “ናይል ኤግልስ ዋን” የሚል ስያሜ የተሰጠው የጋራ የአየር ልምምድ ማካሄዳቸው ይታወሳል፡፡

አሁን ደግሞ ሱዳን እና ግብፅ አቅምን ለማጎልበት እና ልዩ ሀይልን የሚያካትቱ የጋራ ስራዎችን ለማከናወን የታለመው ‘ናይል ኤግል ቱ‘ የሚል ስያሜ ያለው የሁለቱ ሀገራት ወታደሮች የአየር ሀይል ልምምድ ጀምረዋል።

አላማውም የኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴው ግድብ ሙሌትን እና በየኢትዮ ሱዳንን የድንበር ውዝግብ የተመለከተ ነውም ተብለዋል፡፡

የግብፅ ጦር ቃል አቀባይ ብርጋዲል ጄነራል ታመር አል ሩፋይ ረቡዕ ዕለት በሰጡት መግለጫ የሁለቱ ሀገራት ጥምር ጦር በሰሜን ሱዳን በምትገኘው ሜር አየር ማረፍያ ውስጥ ሁለተኛ ዙር ልምምዳቸው እያረጉ መሆናቸው በግልፅ አሳውቀዋል።

ጄነራል ኤል ሩፋይ እንዳሉት ከሆነ ተሳታፊ ኃይሎች የጠላት ኢላማዎችና፤ ለማጥቃትና ወሳኝ ቦታዎች ለመጠበቅ በርካታ የጋራ ልምምዶች ያደረጉ ሲሆን ይሀም ባለ ብዙ ዘርፍ ሃይልን ያቀፈ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በሱዳን የከፍተኛ ድህንነት አካዳሚ የውትድራና ባለሞያና መምህር የሆኑት ሜጀር ጀነራል አሚን እስማኤል እንደተናገሩት በህዳሴው ግድብ ዙርያ የመስማማት እና የመደራደር አንድ አማራጭ አለ። ሁለተኛ አማራጩ ደሞ በግድቡ ላይ የወታደራዊ እርምጃ መውሰድ ነው፡፡

ስለዚ ሁለተኛው አማራጭ የጋራ ልምምድ የሚጠይቅ ሲሆን  የተጀመሩት የጋራ ልምምዶችም ከእነዚህ አማራጮች ውስጥ አንዱ ናቸው ብልዋል፡፡

በሌላ በኩል ሱዳንና ግብፅ ወታደራዊ ልምምድ ማድረጋቸው የኢስላም እንቅስቃሴም ለኢትጵያ መልእክት ለማስተላለፍም ጭምር መሆኑን ኢስማኤል ገልፀዋል፡፡

በእዚሀ ጉዳይ የአለማቀፍ ማህበረሰብ ጣልቃ ካልገባ ሁለቱ ሀገራት ወደ ጦርነት አማራጭ ሊገቡ እንደሚችሉ እጥብቀው ተናግረዋል፡፡

በግድቡና ድንበር ውዝግብን በተመለከተ ኢትዮጵያ ከማንም ሃይል ጋር ጦርነት እንደማትፈልግ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር ዐብይን ጨምሮ ብዙ የመንግስት ባለ ስልጣናት ሲገልፁ ቆይተዋል፡፡

አውሎ ሚድያ መጋቢት 24/ 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ