የጢስ ዓባይ ባህር ዳር የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ መስመር ምሰሶ ስርቆት ተፈፀመበት

0
349

ከጢስ ዓባይ የውሃ ኃይል ማመንጫ ወደ ባህር ዳር የተዘረጋው ባለ 132 ኮሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ መስመር ምሰሶ ላይ ስርቆት መፈፀሙን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገለፀ።

ከሰኞ ምሽት ጀምሮ በተፈፀሙ ስርቆቶች 8 ምሰሶዎች ወድቀዋል፡፡ ይሁንና በአካባቢው ኃይል እንዳልተቋረጠ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

ምሰሶዎቹ በመውደቃቸው ከኃይል ማመንጫው በባህር ዳር ወደ ብሔራዊ የኃይል ቋት ይላክ የነበረ እስከ 30 ሜጋ ዋት ኃይል መላክ አልተቻለም፡፡

ችግሩንም በየደረጃው ለሚገኙ የመስተዳድር አካላት እንዲያውቁት የተደረገ ሲሆን የወደቁትን ምሰሶዎች በመጠገን ወደነበሩበት ለመመለስ የጥገና ስራ መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።

አውሎ ሚድያ መጋቢት 23/ 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ