የናይጀርያዋ አልፓ ጀት ለዘመቻ በሔደችበት ጠፋች ተባለ

0
573

የናይጂርያዋ አልፓ ጀት ተብላ ምትጠራዉ የውግያ አውሮፕላን ለዘመቻ በሔደችበት በትላንትናው እለት መጥፋትዋ ተነገረ፡፡

አውሮፕላንዋ የጠፋቸው ከቦክሀራም  ተብሎ ሚጠራው የአሸባሪ ቡድን ጋር በነበረ ውግያ ሲሆን በሰሜን ምስራቅ ከቦሮና ተብሎ በሚጠራ ግዛት ላይ ነው፡፡ ይህ እንዲህ እንዳለ ጀትዋ በአሸባሪዎች ተመታ ወይም ተይዛ ልትሆን ትችላለች የሚል ግምትም አለ ሲል የገለፀዉ መቀመጫው ኒዉዮርክ ያደረገ ሳህራ ሪፖርተርስ የተባለ አንድ የኦንላይን ሚድያ ነዉ ፡፡

የናይጄርያ አየር ኃይል በበኩሉ አውሮፕላኗ የት እንደገባች ምንም መረጃ እንደሌለዉ ባወጣዉ መግለጫ አሳታዉቋል፡፡

የኤን ኤ ኤፍ የህዝብ ግኑኝነት እና መረጃ ዳይሬክተር የሆኑት ኤድዋርድ ጋብዌት እንዳሉት ከሆነ ጀትዋ በቦርኖ ግዛት ላይ ከ ራዳር ውጭ እስክትሆን የምድር ጦሮችን እርዳታ በማድረግ ላይ ነበረች፡፡

“ጀትዋ ያለችበት ቦታ ወይም እንዴት ከራዳር ዉጪ ሆነች የሚለውን ነገር እስካሁን ማወቅ አልቻልንም ግን ምክንያትዋ እንደታወቀ ለህዝብ ይፋ እናደርጋልን “ሲሉ ኮማንደሩ ገልፀዋል፡፡ ይህ እንዲ እንዳለ የፍለጋና የማዳን ጥረቶች አሁንም እየተከናወነ መሆኑ አክለዋል፡፡

ቦክሀራም የተባለ አሸባሪ ቡድን አሁን ከሳህራ በታች ሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት በዋነኝነት የናጀሪያ ስጋት መሆኑን ቀጥልዋል፡፡

አውሎ ሚድያ መጋቢት 23/ 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ