በአዲስ አበባ ታስረው የቆዩ የትግራይ ተወላጆች በከፊል ተለቀቁ

0
610

ከትግራይ ክልል ወደ አዲስ አበባ ሲገቡ ከአውቶብስ ተወስደው በአንድ ስፍራ ታስረው የቆዩ የትግራይ ነዋሪዎች በከፊል መለቀቃቸው ተነገረ፡፡

ከትግራይ ክልል ጦርነቱ እና ለህክምና ብሎም ለተለያዩ ጉዳዮች ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ ከአውቶብስ እንደወርዱ ተደርገው  ገላን ኮንደምኒየም አካባቢ በሚገኝ የቆርቆሮ አዳራሽ ውስጥ ታሰረው የቆዩ ነዋሪዎች በዋስ መለቀቃቸው ተናግረዋል፡፡

ነዋሪዎቹ መጋቢት 13 ወደ አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን ለ10 ተከታታይ ቀናት ያለ ምንም የህግ አግባብ በአንድ ቦታ እንዲቆዩ መደረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

በስፍራው ተይዘው የቆዩ ታሳሪዎች እንደተናገሩት የአዲስ አበባ የነዋሪነት መታወቂያ እና የህክምና ማስረጃ ያላቸው 36 እስረኞች ተለቀዋል፡፡

በቦታው ተይዘው ከቆዩት ታሳሪዎች  መረጃ መሰረት ታሳሪዎችን የሚጠብቁ፤ ለታሳሪዎችም ሳጅን መሆናቸውን የገለፁ ጠባቂ ጋር አሀዱ ደውሏል፡፡ 

ትእዛዝ የሰጣችው የትኛው የፖሊስ አካል ነው ለሚለው ጥያቄ ግን ምላሻቸው  ስልክ መዝጋት ነበር፡፡

ከስፋራው ከነበሩ ታሳሪዎች በተገኘው መረጃ መሰረት ዋስ ያላገኙ ሰዎች አሁንም በቦታው በእስር እንደሚገኙ ተነግረዋል፡፡

አውሎ ሚድያ መጋቢት 23/ 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ