የUNHCR ምክትል ተወካይ ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ተወሰነ

0
479

የኢትዮጵያ መንግሥት ቅሬታ ያቀረበባቸው የተባባሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት ምክትል ተወካይ የሆኑት ማቲጂስ ሌ ሩቴ ድርጅቱ ከአገሪቱ እንዲወጡ መወሰኑ ተሰማ።

ምክትል ተወካዩ ሩቴ ላለፈው አንድ ዓመት ከሁለት ወር በኢትዮጵያ የድርጅቱ ምክትል ኃላፊ ሆነው በማገልገል ላይ የነበሩ ሲሆን መንግሥት ባቀረበባቸው ቅሬታ ምክንያት ተቋማቸው ከኢትዮጵያ አንስቶ ወደሌላ አገር እንዲዘዋወሩ ማድረጉን ቢቢሲ ከድርጅቱ ሠራተኞችና መንጭ አግኝቻሎ ሲል ዘግቦታል፡፡

የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ተቋም ከፍተኛ ኃላፊ የነበሩት ግለሰብን ጨምሮ ሌሎች የተቋሙ ሠራተኞች ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር በተያያዘ ቅሬታ ማቅረቡን ተገልጸዋል።

በሌላ በኩል በኢትዮጵያ መንግሥት ቅሬታ የቀረበባቸው ምክትል ኃላፊው በተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ተቋም ውስጥ ከ25 ዓመት በላይ ማገልገላቸውን ለማወቅ ተችለዋል። ከዚህ ቀደምም በቡልጋሪያ የስደተኞች ተቋሙ ዋና ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል።

“በአጠቃላይ በተመድ የስደተኞች ድርጅት ውስጥ ያሉ በርከት ያሉ ሠራተኞች ላይ ቅሬታችንን ካስገባን ሰንብተናል። በዚህም ሠራተኞቹ የሚጠበቅባቸውን የፖለቲካ ገለልተኝነት አላሟሉም የሚል ሃሳብ አለን” ሲሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለልጣን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

እኚሁ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣን ጨምረውም በሠራተኞቹ ላይ የተነሳው የገለልተኝነት ጥያቄ በትግራይ ክልል ከተካሄደው ወታደራዊ ግጭት ጋር የተያያዘ መሆኑንም ጭምር ተናግረዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ድርጅት በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጥበት ከቢቢሲ ጥያቄ ቀርቦለት በተቋሙ ሠራተኛ ላይ ቅሬታ መቅረቡን አረጋግጧል።

“የኢትዮጵያ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በአንድ ባልደረባችን ላይ አቤቱታቸውን አቅርበዋል” ሲል ድርጅቱ ለቢቢሲ በሰጠው የኢሜይል ምላሽ ላይ ገልጿል።

አክሎም “ተቋሙ ግለሰቡን ወደ ሌላ ቦታ የመቀየር ሥራ ሰርቷል፤ ይህ ግን ቀድሞውንም እየሰራንበት ከነበረው የመዋቅር ማሻሻል ተግባር ጋር የሚገናኝ ነው” ሲል ድርጅቱ ስለእርምጃው አስረድቷል።

ድርጅቱ በትግራይ ክልል ካጋጠመው ድንገተኛ ቀውስ በኋላ በክልሉ ያለውን ሥራ ለማጠናከር የውስጥ ምክክሮች ሲደረጉ እንደነበር እና የተቋሙን ሰው ኃይል በድጋሚ መልሶ ለማዋቀር እየተሰራ እንደበርም የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት ገልጿል።

አውሎ ሚድያ መጋቢት 22/ 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ