የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ሁለት ኢትዮጵያውያንን ገደሉ

0
538

የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር አካባቢ በሚገኘው ሓምድያት የስደተኞች ስፍራ ወደ ትግራይ ክልል በመመለስ ላይ የነበሩ ሁለት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ገደሉ ተባለ፡፡

በቦታው የነበሩት የአይን አማኞች ለሱዳን ትሪቡን እንደተናገሩት ከሆነ ትላንት ማክሰኞ የኤርትራ ወታደሮች ዲማ በተባለ ቦታ ላይ ሁለት ሰዎች ሲገደሉ ሁለት ሰዎችን አቁስለዋል የተባለ ሲሆን 76 ሰዎች ደግሞ ከጥቃቱ ማመለጣቸውን ተናግረዋል፡፡

እንደዘገባው ከሆነ ተመላሸቹ ከ ከሱዳን ሓምድያት የስደተኞች ማእከል ወደ ትግራይ ክልል ሑመራ በመጓዝ ላይ ሳሉ ነው ጥቃቱ የደሰባቸው ነው የተባለው፡፡

የአይን እማኞች ለሱዳን ትሪቡን እንደተናገሩ ሁለቱም ሟቾች ጭንቅላታቸው በጥይት ተመትተው መገደላቸቅ ታውቋል።

ከጥቃቱ ያመለጡ የተወሰኑ ስደተኞች ጨምሮ ሁለቱ ቁስለኞች ህክምና ለማግኘት ወደ ሱዳን የተመለሱ ሲሆኑ ሁለቱም በተፈፀመባቸው ጥቃት የተገደሉት ደግሞ ሱዳን ዉስጥ እንዲቀበሩ ተደርግዋል ተብሏል፡፡

በሱዳን የስደተኞች ኮሚሽን ማክሰኞ እለት ያወጣው ሪፖርት እንደሚያመለክተው ከሆን በሃምድያት እና መዲና በሚገኙ የስደተኞች ማእከል ከ30ሺ በላይ ሰደተኞች አሉ ተብለዋል፡፡

ኮሚሽኑም ከሁለቱም የስደተኞች ማእከል በተጨማሪም ገዳሪፍ በተባለ ቦታ ተጨማሪ የስደተኞች ስፍራ እንዲሰራም የጠየቀ ቢሆንም ነገር ግን የተባባሩት መንግስትታት የስደተኞች ድርጅት እና በሱዳን የስደተኞች ኮሚሽን ቦታው ታይቶ እና ምክክር ከተደረገ በኋላ ውሳኔ ይሰጠዋል ተብለዋል፡፡

በፌድራል መንግስት እና ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህውሓት) መካከል በተከፈተው ጦርነት ምክንያት ከትግራይ ክልል ተፈናቅለው ወደ ሱዳን ያቀኑ የስደተኞች ቁጥርም ከ 66ሺ በላይ ደርሰዋል፡፡

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መጋቢት 17 ጠዋት ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በአስመራ በአደረጉት ውይይት ኤርትራ ሠራዊቷ ከኢትዮጵያ ድንበር ለማስወጣት መስማማትዋ ቢነገርም እስካሁን ግን ምንም የተለየ ነገር የለም፡፡

የተባበሩት መንግስታት ጨምሮ የሱዳን ከፍተኛ ባለ ስልጣናት የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር እንደሚገኙ ሲገልፁ ቆይተዋል፡፡

አውሎ ሚድያ መጋቢት 22/ 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ