የመቀለ ከተማ ጊዚያዊ ከንቲባ አቶ አታክልቲ ሀይለስላሴ ከስለጣናቸው ለቀቁ

0
719

የጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኒ አባል የሆኑትና የመቀለ ከተማ ጊዚያዊ ከንቲባ ሆነው እያገለገሉ የቆዩት አቶ አታክ ልቲ ሀይለስላሴ በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣኔን ለቅቂያለሁ ብለዋል።

ባለፈው ሳምንት ምሳ በልተው ሲወጡ ከአንድ ሆቴል  የእንጅ  ቦንብ ተወርውሮባቸው ከግድያ አመለጡ የተባሉት አቶ አታክልቲ ከጊዚያዊ ከንቲባነታቸው በራሳቸው ፈቃድ እንደለቀቁ ለአዲስ ስታንዳር አሳውቀዋል።

አቶ አታክልቲ የለቀቁበትን ምክንያት ዝርዝር ዛሬ አሳውቃለሁ ያሉ ሲሆን በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳድር ስር ተመድበው የነበሩ ሀላፊዎች ከስልጣናቸው እየለቀቁ ነው።

ቀደም ሲል የኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ሀላፊው አቶ አምዶም ገብረስላሴና የክልሉ የኮንስትራክሽን መንገድና ትራስፖርት  ቢሮ ሀላፊው አቶ  አሉላ ሀብተአብ ከስልጣን ተነስተዋል።

ሁለቱ ሀላፊዎች ከስልጣናቸው የተነሱት ተባረው ሲሆን የከንቲባ አቶ አታክልቲ ከስልጣን መነሳት ግን በራስ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ነው ተብሏል።

አውሎ ሚድያ መጋቢት 22/ 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ