በትላንትናው ዕለት በምዕራብ ወለጋ ዞን ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቁ ሰዎች መገደላቸው ተሰማ

0
455

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ጋምቤላ ወረዳ፤ ቦኔ ቀበሌ፤ ትናንትና ምሽት 3 ስዓት ላይ በርካታ ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን የአከባቢ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

ነዋሪዎችን አክሎ አሁን ላይ አስከሬኖች በየቦታው ተጥለው መገኘታቸውን ገልፀው ቁጥሩ ምን ያህል ነው የሚለውን ለመግለፅ አስቸጋሪ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

ይህንን በተመለከተ ዛሬ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ባወጣው መግለጫ ግድያው የተፈፀመው በኦነግ ሸኔ ነው ብለዋል፤ በጠፋው የሰው ሕይወትም አዝኛሎ ብለዋል፡፡

ግድያ በተፈፀመበት አካባቢ የህግ የበላይነት ለማስፈን የክልሉ የፀጥታ አካል መሰማራቱንም የክልሉ መንግሥት ባወጣው መግለጫ ተናግሯል፡፡

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉት ነዋሪዎች ለአል-ዐይን እንደገለፁት ከሆነ ‘እኛ የፖለቲካ ሰዎች አይደለንም፤ ገበሬዎች ነን፤ መንግስት ለምን አይደርስልንም?” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

 በከብት ማደለብያና መጠበቅያ ቦታ ላይ ብቻ 20 አስከሬኖች  መገኘታቸውን ያነሱት ነዋሪዎቹ አሁንም ከፍተኛ የድህንነት ስጋት እንዳለባቸው ነው የገለፁት፡፡

የክልል መንግሰት ድርጊቱ በተፈጸመበት አካባቢ በፍጥነት በመድረስ በወሰደው እርምጃ በጥቃቱ አድራሾች ላይ የአጸፋ እርምጃ የወሰደ ሲሆን በቀጣይነትም የሚወሰዱ እርምጃዎችን ለሕዝብ ይፋ እንደምናደርግ ከወዲሁ እንገልጻለን ሲል መግለጫው ያትታል፡፡

አውሎ ሚድያ መጋቢት 22/ 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ