ማህበራዊ ሚዲያ በሀገሪቷ የሚፈጥረዉ የፖለቲካ ተፅዕኖ የጎላ ነዉ ተባለ

0
228

ኢንተርናሽናል ሪቫል  ሚኒስትሪ ባዘጋጀዉ መድረክ የተገኙ ታዳሚዎች በሀገሪቷ ማህበራዊ ሚዲያ የሚፈጥረዉ የፖለቲካ ተፅዕኖ የጎላ ነዉ አሉ፡፡

በዚህ ወቅት ማህበራዊ ሚድያ ከብሮድካስትና ሌሎች መገናኛ ብዙሀን ይልቅ ተደራሽነቱ የላቀ መሆኑንና የሚፈጥረዉ አውንታዊና አሉታዊ ተፅእኖም በዛዉ ልክ መሆኑን ተሳታፊዎቹ ገልፀዋል፡፡

ማህበራዊ ሚዲያ ከላይ ወደ ታች ብቻ ይፈስ የነበረዉን የመረጃ ፍሰት ወደ ጎንዮሽ እንዲፈስ ከማድረጉም በተጨማሪ ዜጎች  የተሰማቸዉንና የያዙትን መረጃ በነጻነት እንዲገለፁ መንገድ መፍጠር የቻለ ነዉ ተብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ማህበራዊ ሚድያ በዚች ሀገር እየተፈጠረ ያለዉን የእርስ በርስ ግጭት በማባባስ ተፅዕኖዉ የጎላ መሆኑ ተሳታፊዎቹ ተናግረዋል፡፡

በመድረኩ ከፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፤ የሲቪል ሶሳይቲ  እና ከተለያዩ ተቋማት የመጡ ተወካዮች ተገኝቷል፡፡

የመድረኩ ሙሉ ይዘት በአዉሎ ዩቱይብ ያገኙታል፡፡

አውሎ ሚድያ መጋቢት 22/ 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ