አባቴ የኤርትራ ወታደሮች እኛ ላይ እንዳይተኩሱ ሲለምናቸው ነበር – ታዳጊ ምብራቅ

0
1059

ምብራቅ ኢሳያስ የ14 እድሜ ታዳጊ ወጣት ስትሆን ዛላምበሳ በምስራቃዊ ትግራይ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር ላይ ከምትገኝ ከተማ ትኖር ነበር፡፡

ፌደራል መንግስት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በሰሜን እዝ ወታዶሮች ላይ ጥቃት ፈፅሞብኛል ማለቱን ተከትሎ ጦርነት ካወጀ ግዜ ጀምሮ ብዙ ንፁሃን ዚጎች ከተገደሉባት ከተማ አንድዋ መሆንዋ ሮይተርስን ጨምሮ ሊሎች ያለማቀፍ ሚድያዎች ሲገልፁ ቆይተዋል፡፡

ጦርነቱን ተከትሎ በቤተሰቦቻቸው እና በራሳቸው ብዙ እንግልተና ስቃይ ከደረሰባቸው እንድዋ ምብራቅ ነች፤ ያሰለፈችው ብዙ የስቃይ ቀናት ስታወራ እንዲ በማለት ታስታውሰዋለች፤ ከቀኑ 6 ሰኣት ላይ ነው ከቤተሶቦቼ ጋር እቤት ነበርን በድንገት የጥይት ቶክስ ሰማን ከትንሽ ቆይታ ቡኋላ የኤርትራ ወታደሮች ቤታችን ድረስ መጥቶ አንኳኩ ክዛ ኣባቴ እንዳይተኩሱ ሲለምናቸው ነበር ያባቴን ልመና ወደ ጎን ትቶ ሦስት ግዜ ደረቱ ላይ በመተኮስ አባቴን ገደሉት፤ እናቴም ከጀርባዋ ተኮስባት በዛች ቅፅበት የኤርትራ ወታደሮች አባቴንና እናቴን ገደልቡኝ ስትል በዛን ስአት የነበረ ሁኔታ ለሮይተርስ ገልፃለች፡፡

የምብራቅ አባት የኢትዮጵያ ኦርተዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታይ እና አገልጋ ቄስም እንደ ነበሩ ልጃቸው ምብራቅ ትገልፃለች፡፡ ይህ አሳዛኝ ክስተት የተፈፀመው ደሞ ጦርነቱ ከተጀመረ ከ10 ቀናት ቡኋላ ነው፡፡

ምብራቅ ወታደሮቹ ቤተቦችዋን ከገደሉባት ብኋላ ከ 1 እስከ 12 እድሜያቸው ሚደርሱ ቤተሰቦችዋ የባታቸውና የናታቸው ሬሳ ላለማሳየት በተጨማሪም ለድህንነታቸው ስትል ካለ ውሃ፤ ምግብ እና መብራት ለሁለት ቀናት አልጋ ስርም ደብቃቸው ነበር፡፡

በቦታው የነበረ ግርግር ትንሽ ረገብ ሲልላት ምብራቅ አምስት ቤተሰቦችዋን ይዛ ዓዲግራት የሚገኙ ቤተሰቦችዋ ይዛቸው ሄደች ሮይተርስ የህክምናዋ ውጤት አይቼዋለሁ ብሎ በድረገፁ እንዳስነበበው ከሆነ ምስራቅ እግርዋን ጭንዋ አካባቢ እንደተመታችና ከቁስልም አልፎ ኢነፌክሽን ፈጥረዋል ነው የተባው፡፡

በተጨማሪም በዓዲ ግራት ዙርያ የሚኖሩ የሃይማት አባት አቡነ ምርሃ ክርስቶስ ለሮይተርስ እንደገለፁት ጦርነቱ ከተጀመረ ጀምሮ ቢንስ 1,151 ቄሶች የምብራቅ ወላጅ አባትን ጨምሮ በወታደሮች ተገድለዋ ሲሉ በእጃቸው ከያዙት የሟቾች ዝርዝር ተናግረዋል፡፡

ከእዚህ ሁሉ ክንውን በኋላ ኤርትራ ሠራዊቷ ከኢትዮጵያ ድንበር ለማስወጣት ተስማማታለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ መግለፃቸው አይዘነጋም።

ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የድንበር አካባቢዎቹን ተረክቦ ጥበቃውን ወዲያውኑ እንደሚጀምር ሁለቱ መሪዎች ከስምምነት ደርሰዋል።

ምንም እንካን ሁለቱም መሪዎች የኤርትራ ወታደሮች ለማስወጣት ቢስማሙም መቼና እንዲት ለሚለው ጥያቄ ግን መልስ አላስቀመጡም፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በትግራይ ከተከሰተው ወታደራዊ ግጭት ጋር ተያይዞ የኤርትራ መንግሥትና ሕዝብ ሠራዊታቸው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በገባበት ጊዜ ላደረገለት ድጋፍ በተለያዩ አጋጣሚዎች በተደጋጋሚ ሲያመሰግኑ ቆይተዋል።

 የኤርትራ መንግስት እሰካሁን ወታደሮቹ ከትግራይ ክልል ስለማስወጣትም  ሆነ ወታደሮቹ በትግራይ ህዝብ ላይ የፈፀሙትን ግፍ እና እንግልት በተመለከተ ከማጣጣል ውጪ ምንም ያለው ተጨባጭ ነገር የለም፡፡

አውሎ ሚድያ መጋቢት 20/ 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ