በኢትዮጵያ የግብረ ሰናይ ድርጅት ሰራተኛ ተገደለብኝ – ጎል

0
588

ላለፉት 37 አመታት ገደማ በኢትዮጵያ የእርዳታ ስራዎችን ሲያከናውን የቆየው ጎል የተሰኘው በአርላነድ ሚገኘው አንድ የግብረ ሰናይ ድርጅት ረቡዕ መጋቢት 15/2013 ዓ.ም በአሶሳ እና ያሶ መካከል በሚገኝ ቦታ ላይ ሰራተኛየ ተገደለብኝ ሲል ትላንት ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡

ድርጅቱ በትላንት መግለጫው እንዳለው፤ ጥቃቱን የተፈጸመው  በወለጋ ዞን  ሲሆን ማንነታቸው ያልታወቀ 12 ታጣቂዎች ናቸውም ብለዋል ። ታጣቂዎቹ   በጉዞ ላይ የነበረ የድርጅቱን መኪና ካስቆሙ በኋላ ሾፌሩን እና የድርጅቱን ሰራተኛ አግተው ወደ ጫካ መውሰዳቸውንም አመልክቷል።

“ታጣቂዎች ከነበሩበት መኪና አስወርዶ ጥያቄ ከተጠየቁ በኋላ፤ አሽከርካሪው በጥይት ተመቶ ሲገደል ሊላኛው ሰራተኛ ለማምለጥ ችሏል ሲል ድርጅቱ  በመግለጫው አስታውቀዋል። “ፈታኝ በሆነ ከባቢ ውስጥ የተቸገሩ ተጋላጭ ማኅበረሰቦችን ለመርዳት ሥራቸውን በሚያከናውኑ የሰብዓዊ ዕርዳታ ሠራተኞች ላይ የተፈጸመውን ይኸን ግድያ አጥብቀን እናወግዛለን። ይህ ጥቃት በትዕግስት ሊታለፍ አይገባም” ሲል ለሟች ቤተሰቦች ሀዘኑን በገለጸበት መግለጫ አውግዟል።

ጥቃት የደረሰባቸው ሰራተኞች ወደ ስፍራው የተጓዙት በአካባቢው የሚፈለገውን የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ሁኔታ ለመገምገም እንደነበር የግብረ ሰናይ ድርጅቱ ጠቁሟል። በኪራይ አገልግሎት ይሰጥ ነበር በተባለው የድርጅቱ ተሽከርካሪ፤ የዕርዳታ ድርጅቱ መለዮ፤ የሚለጠፍ ባንዲራ እና የጦር መሳሪያ እንዳልተጫነበት የሚጠቁም ምልክት እንደነበረው ተቋሙ ገልጿል። ታጣቂዎቹ በተሽከርካሪው ውስጥ የነበረውን ንብረት ከወሰዱ በኋላ በእሳት እንዳጋዩትም መግለጫው አክሏል። 

በሰራተኛው ላይ ስለተፈጸመው ጥቃት ተጨማሪ መረጃ እያሰባሰበ እንደሚገኝ የገለጸው የግብረ ሰናይ ድርጅቱ፤ “ግድያው በክልሉ የሰብዓዊ ዕርዳታ ሰራተኞች የሚገጥማቸውን አደጋ ያሳያል” ብሏል። ታጣቂ ቡድኖች “የሰብዓዊ ዕገዛ አቅርቦትን ማክበር አለባቸው” ሲልም አሳስቧል።  

ጥቃቱን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ከአካባቢው ባለስልጣናት ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን በመግለጫው የጠቆመው ድርጅቱ፤ በኢትዮጵያ “የግብረ-ሰናይ ሰራተኞችን ደህንነት እና ጸጥታ ለማረጋገጥ የባለስልጣናቱ እና ማህበረሰቡ አፋጣኝ እርምጃ ያሻል” ሲል አጽንኦት ሰጥቷል።

አውሎ ሚድያ መጋቢት 18/ 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ