የኤርትራ ጦር በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር ስለመስፈሩ መረጃው የለኝም – አምባሳደር ዲና

0
731

የኤርትራ ጦር በኢትዮ – ሱዳን ድንበር ሰፍሯል ስለተባለው ጉዳይ መረጃው እንደሌላቸው አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለፁ !

ከአንድ ቀን በፊት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኤርትራ ጦር ሱዳን እና ኢትዮጵያ በሚወዛገቡበት የአል-ፋሽጋ አካባቢ መስፈሩን የሚገልፅ ሪፖርት ማውጣቱ ይታወሳል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ አውጥቶ በነበረው ሪፖርት የኤርትራ ጦር በአል-ፋሽቃ ትሪያንግል መስፈሩን እንደደረሰበት ገልጿል።

በዚህ ጉዳይ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ የለኝም ብሏል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ከአሃዱ ሬድዮ ጣቢያ 94.3 ስለጉዳዩ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ ፥ የኤርትራ ጦር ሠራዊት በትግራይ ክልል ፈፅሟቸዋል የተባለው የመብት ጥሰቶች የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እንዲሁም በተባበሩት መንግስታት ድርጅትም በኩል እንዲጣራ ፈቃድ መስጠቱን አስታውሰው ፥ ይኼኛው ጉዳይም በተመሳሳይ መልኩ መጣራት ይችላል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በዋናነት ግን የኤርትራ ጦር በኢትዮ – ሱዳን ድንበር ሰፍሯል ስለተባለው ጉዳይ መረጃው እንደሌላቸው ለሬድዮ ጣቢያው ገልፀዋል።

አውሎ ሚድያ መጋቢት 17/ 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ