ብሔራዊ መግባባት ላይ እሰራለሁ – ህብር ኢትዮጵያ

0
560

ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ ተሳታፌ የሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች አንድ የሆነው ህብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የፓርቲውን ማኒፌስቶ ለህዝብ ይፋ አደረጉ፡፡

በግንቦት እና ሰኔ ወር ላይ ሊካሄድ ቀጠሮ የተያዘለት አጠቃላይ ምርጫ አሳታፊ ባይሆንም ውስጥ ሁነን ለመታገል ወስነናል ያሉት የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ግርማ በቀለ ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ ሁን ባለችበት ሁኔታ ምርጫ ለማካሄድ በቂ ቁመና ባይኖራትም የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አካሄዳሎ ባለው ምርጫ ለመሳተፍ ወስነናል ብለዋል ሊቀመንበሩ፡፡

ፓርቲው ማኒፌስተው ለጋዜጠኞች ሲያቀርቡ በሀገራዊ መግባባት ላይ ትኩረት አድርገው እንደሚያስቡ አሳውቋል፡፡

ሃገሪትዋ አሁን ወዳለችበት አለመግባባት ላይ የደረሰችው ብሄራዊ መግባባት ላይ ስላልተሰራ ነው የሚል አቋም አላቸው፡፡

ብሄራዊ መግባባት እና አንድነት ላይ  ከተሰራ ማህበራዊና ኢኮኖሚዊ ችግሮችን በቀላሉ መፍታት እንደሚችሉ የፓርቲው የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ተናግርዋል፡፡

ህብር ኢትዮጵያ 280 እጩዎችን ለማስመረጥ ያስመዘገበ ሲሆን በቤንሻንጉል እና ኦሮሚያ ክልል ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት አባሎቻችን አናወዳድርም ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ፋና ነጋሽ

አውሎ ሚድያ መጋቢት 17/ 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ