በግጭቱ ተዘግቶ የነበረው የአዲስ አበባ-ደሴ መንገድ በመከላከያ አጃቢነት መከፈቱ ተገለጸ

0
446

ላለፉት 8 ቀናት ተዘግቶ የነበረው የአዲስ አበባ ደሴ መንገድ በሀገር መከላከያ ሰራዊት አጃቢነት መከፈቱን አል ዓይን በድረገፁ አስነብቧል።

ይህ መስመር ከ 8 ቀናት በፊት መጋቢት 10 ቀን 2013 ዓ/ም በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እና ልዩ ቦታው አጣዬ ከተማ እና ዙሪያ ባሉ የኦሮሞ ብሄረሰብ አሰተዳደር ዞን አካባቢዎች በተፈጠረው ግጭት ነበር የተዘጋው።

በአካባቢው በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሚያስኬደው ዋናው መንገድ ከሸዋሮቢት እስከ ከሚሴ ከተማ ድረስ በመዘጋቱ የጸጥታ ስራውን ሲያደናቅፍ እንደነበር ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ በመከላከያ ሰራዊት አጃቢነት ሚኒባሶች የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች መገለፃቸውን አል ዓይን አስነብቧል።

ግጭት በተከሰተባቸው ከሸዋሮቢት እስከ ከሚሴ ከተማ ድረስ ባሉ አከባቢዎች የመንግስት ተቋማት ፣  ባንኮች እና ሌሎች የንግድ ድርጅቶች ዝግ መሆናቸው ተገልጿል።

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እና ልዩ ቦታው አጣዬ ከተማ እና ዙሪያ ባሉ የኦሮሞ ብሄረሰብ አሰተዳደር ዞን በተፈጠረው ግጭት የበርካቶችን ህይወት ሲያልፍ እስካሁን ግምቱ ያልታወቀ ንብረት ወድሟል።

በአጣዬ፣ ጀውሃ፣ በካራቆሪ፣ በማጀቴ፣ በከሚሴና በሸዋሮቢት ግጭቱ የቆመ ቢሆንም አሁንም ነዋሪዎች ግጭቱ መልሶ ሊከሰት ይችላል፤ በአካባቢው በቂ የጸጥታ ሃይል የለም ሲሉ ስጋታቸውን ለዜና ማሰራጫው ተናግረዋል።

ትላንት ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ አላላ እና በአሽኳይ ሸረፋ ቀበሌዎች ላይ በተፈፀመ ጥቃት ሰዎች መገደላቸው ንብረት እንደወደመ ነዋሪዎች መናገራቸውን አል ዓይን (Al Ain) በድረገፁ አስነብቧል።

አውሎ ሚድያ መጋቢት 17/ 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ