በትግራይ ክልል ውስጥ ከ500 በላይ ሴቶች ተደፍረዋል – ተ.መ.ድ

0
986

በትግራይ ክልል ውስጥ ጦርነቱ ተከትሎ ከ 500 በላይ ሴቶች መደፈራቸው ከ5 ጤና ጣብያዎች ሪፖርት የተደረጉ መረጃዎች ደርሰውኛል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይፋ አደረገ፡፡

የተባበሩ መንግስታት ሀሙስ እለት ባወጣው መግልጫ መሰረት የህክመና አገልግሎትና በማጣትና ሊሎች ጥቃቶች ምክንያት ተጠቂዎች ቁጥራቸው ከፍ ሊል እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የእርዳታ አስተባባሪ የሆኑት ዋፋ ሴቶች በታጣቂዎች መደፈራቸውን ገልጸው በቡድን አስገድዶ መድፈር፤ ቤተሰቦቻቸው ባሉበት አስገድዶ መድፈር እንዲሆም  ወንዶቹን በቤተሰቦቻቸው ጥቃት እንዲሰነዝሩ ተገደዋል ብለዋል በኒው ዮርክ ውስጥ ለተባበሩት መንግስታት አባልሃገራት በሰጡት መግለጫ፡፡

በመቐለ፤ ዓዲግራት፤ ውቕሮ፤ ሽረና አክሱም በሚገኙ አምስት የህክምና ተቋማት ቢያንስ 516 የአስገድዶ መደፈር ክሶች ሪፖርት መደረጋቸው አስታውቀዋል፡፡ አክለውም አብዛኛው የጤና ተቋማት አገልግሎት የማይሰጡ ከመሆናቸው በተጨማሪም ከአስገድዶ መደፈር ጋር ተያይዞ የሚመጡ መገልልና ሌሎች ነገሮች አንፃር ሲታይ ከዚም በእጅጉ ሊበልጥ እንደሚችል ነው የተናገሩት፡፡

በቁጥር ብዛት ያላቸው የተባበሩት መንግስታት ባለስልጣናት በትግራይ ክልል ሰላማዊ ዜጎች ላይ እየደረሰ ስላለው ጥቃት ለማስቆም ባለፈው ሰኞ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡  በተለይም አስገድዶ መድፈርና ሊሎች አሰቃቂ የወሲብ ጥቃቶች መንግስት በገለልተኛ አጣሪ ቡድን ማስመርምር እንዳለበትም ውሳኔ አሳልፈው ነበር፡፡

ጠቅላይ ሚኒሰተር ዶ/ር ዐብይ አሕመደ ለፓርላማ አባላት የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ክልል ውስጥ መኖራቸው አምነው እነዚ ጥቃቶችንና ሊሎች ኢሰብአዊ የሆኑ ድርጊቶችን በተመለከተ  እንዳሉት ከሆነ የኤርትራን ወታደር፤ የኢትዮጵያ ወታደርን ጨምሮ ሊሎች ሃይሎች በዚ ጉዳይ ላይ ጥፋት ካጠፉ ተጠያቂ ከመሆን አያመልጡም ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በተቃራኒው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በእዚህ ሳምን ባወጣው ሪፖረት መሰረት የኤርትራ ወታደሮች በአክሱም ከተማ ላይ በንጹሃን ዜጎች ላይ የደረሰው ጭፍጨፋ የኤርተራ መንግስት ውሸት ነው ሲል ማጣጣሉም የሚዘነጋ አይደለም፡፡

በእዚህ ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስተሩ እንደ አስገድዶ መድፈር ያሉ ጭካኔዎች መከሰታቸውን ለመጀመርያ ጊዜ አምነው ማነኛውንም ወንጀል የሚፈፀሙ ወታደሮች ቅጣት አንደሚወስዱ ተናግረዋል፡፡

የኤርትራ ወታደሮች ንፁሃን ሰዎች በመግደላቸው፤ በቡድን ሴቶችን መድፈራቸው፤ የቤተሰብ አባላት በማሰቃየት እንዲሁም ሰብሎችን መዝረፍ ላይ  እንደሚገኙ በቁጥር ብዛት ያላቸው ሰዎች ነገሩኝ ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

አውሎ ሚድያ መጋቢት 17/ 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ