የባልደራስ አመራሮች አፋጣኝ ፍትሕ ይሰጠን ሲሉ ፍርድቤትን ጠየቁ

0
248
Renowned Ethiopian journalist, Eskinder Nega, has been imprisoned nine times simply for doing his job. He was released earlier this year after spending his longest stint in prison.

አፋጣኝ ፍትሕ ስጡን እና ከእስር ቤት ወጥተን ለምርጫው አስተዋፅኦ ማድረግ እንፈልጋለን” – አቶ እስክንድር ነጋ

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አመራሮች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል ፣ አስቴር ስዩም እና አስካለ ደምሌ ትላንት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ችሎት ቀርበው ነበር።

ፍርድ ቤቱ ብይን መስጠት የሚችለው የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ ካወቀ በኋላ እንደሆነ በመጥቀስ ለሚያዝያ 11 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የሚዳኘው የይግባኝ ችሎት መጋቢት 28 ቀን 2013 ዓ.ም ስድስት ኪሎ በሚገኘው የጠቅላይ ፍርድ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይካሄዳል።

የባልደራስ ፕሬዚደንት አቶ እስክንድር ነጋ ዐቃቤ ሕግ ይግባኝ የጠየቀበት ሰነድ ግልባጭ እንዲሰጣቸው በትላንት ችሎት ቢጠይቁም እንዳልተሰጣቸው ተገልጿል።

ዐቃቤ ሕግ በሰዓቱ ሰነዱን አለመያዙን ገልፆ በሌላ ጊዜ እንደሚሰጣቸው ቃል እንደገባላቸው ተነግሯል።

አቶ እስክንድር ፥ “አሁንም እድሎች ሙሉ በሙሉ አላለፉም፤ አፋጣኝ ፍትሕ ስጡን እና ከእስር ቤት ወጥተን ለምርጫው አስተዋፅኦ ማድረግ እንፈልጋለን” ጠይቀዋል።

የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዳኞች በበኩላቸው ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ አፋጣኝ ምላሽ ከሰጠ እነርሱም ፈጣን ብይን እንደሚሰጡ ገልፀዋል።

አቶ ስንታየሁ ቸኮል ወቅቱ ዐብይ ፆም የሚጾምበት መሆኑን ጠቅሰው የምልኮ ስፍራ ወዳለበት የእስር ቤቱ ክፍል (ዞን) አራቱንም የህሊና እስረኞች እስር ቤቱ እንዲያዘዋውራቸው ጠይቀዋል። ይህ ካልሆነ በያሉበት የአምልኮ ስፍራ እንዲሰጣቸው ፍርድ ቤቱ ወህኒ ቤቱን ያዝዝ ዘንድ አሳስበዋል።

እምነታቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በምትፈቅደው መሰረት በፀበል ቅዱስ መፈወስ እንደሚፈልጉ የጠቆሙት አቶ ስንታየሁ ፀበል እንዲገባላቸው ጠይቀዋል።

ከዚህ በፊት ቤተሰቦቻቸው ያመጡትን ፀበል ወህኒ ቤቱ አላስገባ ብሎ መልሶታል።

ወ/ሮ አስቴር ስዩም በበኩላቸው “የመደመር መንገድ የተባለው የጠቅላይ ሚንስትሩ መፅሐፍ እስር ቤት ውስጥ እየገባ ነው። ‘ሀገር ስታምጥ’ የተሰኘውን የእኔን መፅሐፍ ግን ማስገባት አልቻልኩም። ተከልክያለሁ። ለምን?” ሲሉ ጠይቀዋል።

ምንጭ፦ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ

አውሎ ሚድያ መጋቢት 16/ 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ