ኢትዮጵያ ያሏት መንገዶች ከሰሀራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት የደረጃ መመዘኛ በታች ነው ተባለ

0
421

ኢትዮጵያ ያሏት መንገዶች ከሰሀራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት የደረጃ መመዘኛ በታች መሆኑን ተነገረ፤ ኢትዮጵያ አሁንም መመለስ  አለባት ተብሎ ከሚጠበቁ የልማት ስራዎች ዉስጥ አንዱ የመንገድ ልማት እና ጥራታቸዉን የጠበቁ የመንገድ ፕሮጀክቶች ተጠቃሽ ናቸዉ፡፡

ኢትዮጲያ ያሏት የመንገድ ሀብቶች የጥራት ችግር የሚነሳባቸዉ እና ተደራሽነታቸዉ አጥጋቢ አለመሆኑ ሲጠቀስ ይስተዋላል፡፡

የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የመንገድ ግንባታ እና የጥራት ደረጃን በአለም አቀፍ ደረጃ ለመገንባት በ10 አመቱ የልማት እቅድ መካተቱን ጠቅሰዋል፡፡

ይህን የ10 አመት እቅድ መሰረት በማድረግም አሁን ኢትዮጵያ ያላትን የመንገድ ሀብት ምልከታ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

በተደረገዉ ምልከታም ያለን የመንገድ ሀብት በአለም አቀፍ ደረጃ ምን ጋር እንደሆንን ያሳያል የሚለዉ በትኩረት መታየቱን ገልጸዋል፡፡

እንደ ሀገርም በአጠቃላይ በመንገድ መሰረተ ልማት በአለም አቀፍ መለኪያዎች ኢትዮጵያ ከሰሀራ በታች ለባሉ የአፍርካ  ባለ ደረጃ ላይ በታች እንደሆነች አይተናል ይሄም በተጨባጭ መንገድ የሌለን ሀገር እንደሆንን አመላክቷል ሲሉ ሚኒስትሯ  ገልጸዋል፡፡

ይህ ምልከታ እንደ ሀገር  ያለንበትን ደረጃ በግልጽ ያመላከተ በመሆኑ ይህን ለመለወጥ እስካሁን በመጣንበት መንገድ ብቻ ለዉጥ ማምጣት እንደማይቻል ታምኖበታል ብለዋል፡፡

በዚህም የአካሄድ ለዉጥ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበታል ብለዋል፡፡

በታቀደዉ የአካሄድ ለዉጥም ክልሎች የአስፓልት መንገድ መገንባት የሚያስችላቸዉ አቅም መፍጠር፤ በፌደራል ደረጃም ሀገርን ከሀገር እና ክልልን ከክልል ለማገናኘት የሚገነቡ መንገዶችን እንዲሰሩ የስራ ክፍፍል  ማድረግ የታመነበት አቅጣጫ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ይህም በተግባር እንዲረጋገጥ የሚያስችል ጥናት ተሰርቶ መጠናቀቁን ሚኒስትሯ አስታዉቀዋል፡፡ አሐዱ ራዲዮ

አውሎ ሚድያ መጋቢት 16/ 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦ https://t.me/awlomedia
ትዊተር፦ https://twitter.com/AwloMedia

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCFRuICCV8fHJGa3AbcA3zOA
ድረ ገጽ፦ https://awlomediatv.com/category/zena/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/awlomedia

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ