ዶ/ር አብይ የኤርትራ ወታደር በ ትግራይ ክልል ውስጥ እንዳለ አመኑ

0
1129

በፊደራል መንግስትና ሕውሓት መካከል ባለው ጦርነት የኤርትራ ወታደር መሳተፋቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ስ ዐብይ አህመድ ለተወካዮች ምክርቤት ገልፅዋል፡፡

የኤርትራ ወታደር ወደ ትግራይ ክልል የገባበት ምክንያትም ሕውሓት በተደጋጋሚ ወደ ኤርትራ ሮኪት ሲተሱ ስለነበረ ነውም ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በትግራይ ክልል የነበሩትን ስራዎችን በጋራ እየገመግሙ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

በተለያዩ ምክንያቶች ሕውሓት ጦርነቱ አሁግራዊ ለማድረግ ለኤርትራ መንግስት ሲጋብዝ ነበር ፤ ለዚህም የኤርትራ ወታደር ወደ ትግራይ ክልል ገብቶ ብዙ ጥፋት እንዳጠፋ ይታማል ሁኖም የኤርትራ መንግስት ለ 20 አመታት ሲጠብቀው የነበረው ድምበር ላይ መሆኑን የኤርትራ መንግስት ገልፆልናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግርዋል፡፡

ይህም የሆነበት ምክንያት የኤርትራ መንግስት ስለ ብሄራዊ ድህንነቴ ያሳስበኛል በሚል ምክንያት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስተሩ ገልፅዋል፡፡

የኢትዮጵያ ወታደሮች ፊታቸው አዙረው ህዝቡን ከኤርርተራ ወታደር እንዳይጠብቁ ከኋው የሚውጋው ሃይል ስላለ ነው በማለት የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒርትሩ ሁኖም የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ህዝብ ላይ የ ሰብአዊ መብት ጥስት ከፈፀሙ ተገቢ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው የኤርትራ መንግስት ገልፆልናል ሲሉ ተናግረዋል።

የኤርትራ ወታደር ድንበር ጥሶ በኛ ህዝብ ላይ ሚያረገው ጥፋት በማነኛውም መንገድ አንቀበልም ይህን ማንቀበለው የ ኤርትራ ወታደር ስለሆነ ሳይሆን የኢትዮጵያም ጭምር ቢያርገው ተቀባይነት የለውም ፤ ዘመቻው በግልፅ ከተለዩ ጠላቶች እንጂ ከ ህዝብጋ አይደለም ፣ ይህ በሚመለከት ከ ኤርትራ መንግስት ጋር በተደጋጋሚ ጊዜ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በመላክ ስንነጋር ነበር ብለዋል።

ኤርትራ የራሷ ጥያቄ አላት ያሉት ዶ/ር አብይ “የኤርትራ ወታሮች የኢትዮጵያ ድንበር አልፎ በሚገኙበት አከባቢዎች ላለፉት 20 አመታት በኤርትራና ኢትዮጰያ ድንበር መካከከል የነበረ ምሽግ ለቃቹ ሂዳችዋል የ ሕውሓት ሓይል ላለፉት 20 አመታት ግፍና እንግልት ሲፈፅምብን ነበር ፤ በተጨማሪም ወደ ውግያ እንድንገባ ሮኬት ሲተኩስ ነበር አሁን ደግሞ እናነንተ ይህን ለቃቹ ወደ መካከለኛው ትግራይ ሄዳቸሁ ጠላት ስታጠቁ ተመልሶ ወደኛ ሊመጣ ይችላል ሆኖም የሃገራችን ሃገራዊ ደህንነት ስጋት አለብን ለዚህ ብለን ድምበር አባቢ ሚገኙ ቦታዎች ይዘናል ነገር ግን የናንተ ወታድር ስራውን ለይቶ ምሽጉን መቆጣተር ከቻለ ክዛ በኋላ እኛ የለንም መቆየት አንፈልግም” ብለውኛል ነው ያሉት

የ ኤርትራ ወታደር በመዝረፍ ይታማል በሚለው ጉዳይ ለኤርትራ መንግስት አቅርበናል የኤርትራ መንግስት በከፍተኛ ሁኔታ ይኮንነዋል ወታደሮችም ካጠፉ እርምጃ ወስዳሎ ብለዋል፡፡

ዶክተር አብይ የኤርትራ መንግሰትና ህዝብ ውለታ አለብን የሰሜን እዝ ሲጠቃ ወደ ኤርትራ ሸሽቶ ቷከፍተኛ ሁኔታ አደጋላይ የወደቀውን የኤርትራ መንግሰትና ህዝብ ተንከባእቦ ወደ ሚፈልገው መልሶልናል የህ በችግር ጊዜ የተደረገልን ውለታ ነው ልንረሳው አይገባም ሲሉም ለምክር ቤብት አባላት ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኤርትራ ሀይል በትክክል መቼ ሊወጣ ይችላል የሚለውን ግን አላነሱም።

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ