የዋጋ ግሽበት ዝቅተኛውን የህብረተሰብ ክፍል እየጎዳ ነው

0
346

የዋጋ  ግሽበት ዝቅተኛውን የህብረተሰብ ክፍል እየጎዳ  መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አህመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት ተናግረዋል፡፡

የዋጋ  ግሽበት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን  ዜጎች   የምግብ ነክ  ወጪ ከ54  እስክ  60 በመቶ ገቢያቸውን ይወስድባቸዋል፣ ቤት ኪራይ  እና አልባሳት ደግሞ ለዋጋ  ንረቱ መንስኤዎች መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

ሰው ሰራሽ እጥረት የሚፈጥሩ ነጋዴዎች አሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣የምርት እጥረት እና አለም አቀፍ ሁኔዎችም ለኑሮ  ውድነቱ መባባስ ችግሮች ናቸው ብለዋል፡፡

የውጭ ገበያ ምርት

የኢትዮጵያ ውጭ ምርት ገበያ  21 በመቶ አድገት አሳይትዋል  ሲሉ  ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡

ከዚህ ቀደም የነበረው የንግድ ሚዛን ልዩነት እየጠበበ መጥቷል ፣ይህም የወጪምርት ገበያ መጨመርእና የገቢ እቃዎች ላይ በሚደረግ ቁጥጥር ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ የንግድ ሚዛን ልዩነትን ከዜሮ በታች በ4  በመቶ እንዲቀንስ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡

ባለፉት  8  ወራት  191  ቢሊዮን ብር ከአገር ውስጥ ገቢ ማስገባት ተችሏል፣ ይህም ባለፈው ዓመት ከተመዘገበው  228  ቢሊዮን ብር ገቢ አንጻር ከፍተኛ መሆኑንም ጠቅላይሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ አገሪቱ ያለባትን የውጭ እዳ ጫና ባለፉት  3 ዓመታት ከነበረበት  37.6 በመቶ አሁን ላይ ወደ  26.8 በመቶ ዝቅ እንዲል በማድረግ ኢትዮጵያ የመበደር አቅሟ መስመር እንዲይዝ የማድረግ ቁመና ላይ እንደምትገኝ ጠቅላይሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

እንደ ጠቅላይ ሚኒሰተሩ አገላለፅ አሜሪካ አውሮፓ በኮረና ምክንያት አድገት ባላሳዩበት ጊዜ ነው ኢትዮጵያ እሂን ለውጥ ያመጣችው፡፡

ኢትዮጵያ ብአለም አውንታዊ አድገት ያሳዩ ካሉ  ያዓለም ሃገራት ተርታ ስምዋ በቀዳሚነት የተጠራ ይገኛልም ብለዋል፡፡

ይሁንጂ ሃገሪትዋ የዋጋ ንረት፤ የምግብ አቅርቦትና ሊሎች ተዛማች ችግሮች አንዳላት ህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት ተናግረዋል፡፡

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ