የኮቪድ19 ወረርሽኝ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

0
301

 የኮቪድ19 ወረርሽኝ አሁንም በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ባሳለፍነው ሳምንት ከነበረው የቫይረሱ የመያዝ አቅም እና በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ መሆኑንም ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል።

በዚህም ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ ከ13 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ በስምንት ቀናት ውስጥ ብቻ ከ118 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ነው ያሉት።

ይሁንጂ የፅኑ ህሙማን ቁጥርም ባለፈው ሳምንት ከነበረት 460 ወደ አሁን ላይ ከ600 በላይ ማሻቀቡም ተነስቷል።

ይህንን ተከትሎም ለፅኑ ህሙማን አጋዥ መተንፈሻ የኦክስጅን እጥረትን ለመፍታት እየሰራ ቢሆንም ህብረተሰቡ የራሱን የመከላከል ሃላፊነት መውሰድ እንዳለበትም ተነስቷል።

ከዚህ በኋላ ሊኖሩ የሚችሉ ስብሰባዎችን ማስቀረት ሳይሆን የኮቪድ19 መከላከል በሚያስችል መልኩ መሆን እንዳለበትም ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ኮቫክስ ፋሲሊቲ አመክኝነት 2.2 ሚሊዮን ዶዝ ክትባት ወደ ሃገር ውስጥ አስገብታ  መንግስትም በይፋ ክትባቱ የመሰጠት ስራ አንዳስጀመረ ይታወሳል፡፡

አስከ ባለፈው ሳምንት ሃሙስ ድረስ 1400 ሰዎች ብቻ የተከተቡ ሲሆን ከተከተቡ ውስጥ የጎንዮሽ ጉዳቶች ሮፖርቶችም 35 ደርስዋል ሲል የምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ገልፀዋል፡፡

ህብረተሰቡም የዚ ጥቅም ተረድቶ ክትባቱ በመውሰድ ራሱን ከ ኮረና መጠበቅ አንዳለበት ተገልፀዋል፡፡

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ