ሀገራዊ ምርጫ ማካሄድ ይቻላል ሲል የጤና ሚኒስቴር ምከረ ሀሳብ አቅርቧል

0
269

በኮቪድ 19 ምክንያት ተራዝሞ የነበረው ሀገራዊ ምርጫ አሁን ላይ ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልቶ ማካሄድ እንደሚቻል የጤና ሚኒስቴር ምከረ ሀሳብ አቀረበ

 በኮቪድ 19 ምክንያት ተራዝሞ የነበረው ሀገራዊ ምርጫ አሁን ላይ ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልቶ ማካሄድ እንደሚቻል የጤና ሚኒስቴር ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክረ ሀሳብ አቀረበ።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምላሽና ቀጣይ እርምኝጃዎች በሚመለከት ለምክር ቤቱ ሪፖርት እና ምክረ ሀሳብ አቅርበዋል።

በቀረበው ሪፖርት እና ምክረ ሀሳብ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስርጭት እየቀነሰ ባይሆንም የቅድመ መከላከል እና ስርጭቱን በመግታት ሂደት ውስጥ በሁሉም ደረጃ አቅም ማሳደግ መቻሉን ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በሁሉም ክልሎች የተሰራጨ ሲሆን፥ በሀገር አቀፍ ደረጃ የኮቪድ 19 በሽታ ከገተኘባቸው ውስጥ 95 በመቶ የታወቀ የጉዞ ታሪክ የሌላቸው መሆኑ ተረጋግጧል ብለዋል።

እስከ መስከረም 6 2013 ዓ.ም ድረስ 1 ሚሊየን 165 ሺህ 647 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በዚህም 66 ሺህ 224 ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱን እና 1 ሺህ 45 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ማለፉንም አስታውቀዋል።

አሁን ላይ የመመርመርም ሆነ ክትትል የማድረጉ አቅም በማደጉ በነሃሴ ወር ብቻ ከፍተኛ የሚባል ቁጥር ያላቸውን ሰዎች ቤት ለቤት መጎብኘት መቻሉን እና ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን መለየት እንዲሁም ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ማከናወን መቻሉንም በሪፖርቱ ላይ አብራርተዋል።

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስርጭትን በተሻለ ከማወቅ በተጨማሪ የመከላከል እና የመቆጣጠር አቅምን በከፍተኛ ደረጃ መፍጠር መቻሉንም ገልፀዋል።

ከእነዚህ ውስጥ አመራሩ ትኩረት አንዲሰጥ ማድረግ መቻሉ፣ በሚዲያ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ መከናወኑ፣ የቅኝት ስራ ላይ የሚያስፈልጉ አደረጃጀቶችን ማስፋት መቻሉ እንዲሁም ከ10 ሺህ 500 በላይ የድንገተኛ ምላሽና የበሽታ ቅኝት የሚከናውኑ ቡድኖችን ማደራጀት መቻሉንም አስታውቅዋል።

የላቦራቶሪ ናሙና መሰብሰቢያ ቦታዎችን በየወረዳው መስፋት መቻለኩንም በሪፖርታቸው አንስተዋል።

የምርመራ አቅም በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ ተችሏል ያሉት ዶክተር ሊያ፥ የጤና ተቋማትና የአልጋ ቁጥር ማሳደግና የቤት ውስጥ ህክምና አገለግሎት ማስጀመር መቻሉንም አንስተዋል።

የመመርመሪያ ኪቶች ማምረቻም ማቋቋም እንደተቻለም በሪፖርታቸው ላይ አቅርበዋል።

በዚሁ መሰረት የቀጣይ ወራት ትንብያ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር፣ የሞት ቁጥር እና ወረርሽኙ ከፍተኛውን ጣሪያ የሚደርስበት ጊዜ በዋናነት የሚወሰነው በአካላዊ መራራቅ እንዲሁም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምበል በሚተገበርበት ደረጃ ነው ብለዋል።

ለምሳሌ ያክል አካላዊ ርቀት 5 በመቶ እና የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ 50 በመቶ የህብረተሰብ ክፍል ውስጥ መተግበር ከተቻለ ምንም አይነት እርምጃ ባይወሰድ ሊደርስ ከሚሽለው የበሽታ ስርጭት እና ሞት አንጻር በ92 በመቶ መቀነስ እንደሚቻል ተመላክቷል።

እነዚህና ሌሎችም ነጥቦችን ታሳቢ ያደረጉ በርካታ እርምጃዎች ሲወሰዱ የቆዩ ሲሆን፥ በቀጣይም በተሻለ ደረጃ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

በዚሁ መሰረት ሀገራዊ ምርጫን የማካሄድ ሂደት ውስጥ በርካታ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች ምልከታ የተደረገባቸው ሲሆን፥ በአንዳንዶቹ በወረርሽኝ ወቅት ምርጫ ተካሂዷል፤ በአብዛኞቹ ደግሞ እንዲተላለፍ ተደርጓል።

በኢትዮጵያም በሽታውን የመከላከልም ሆነ የመቆጣጠር ዝግጅነቱ ዝቅተኛ በነበረበት ወቅት ምርጫን ማከናወን ስጋቱ የበለጠ የሚያሳድገው በመሆኑ በተላለፈው ውሳኔ እንዲራዘም መደረጉ ይታወሳል።

ወረርሽኙ አሁንም የጤና ስጋት ቢሆንም ቀደም ሲል ከነበሩት ለምዶች እንፃር ከፍተኛ አለመሆኑ፣ ኮቪድ 19 በሽታ ረዘም ላለ ጊዜ አብሮን ሊቆይ ሰለሚችልና አንፃራዊ በሆነ ሰዓት ምርጫው ሲራዘም ከነበርንበት ሁኔታ ለስርጭቱ የተሻለ መረጃ ያለን በመሆኑ ቀደም ሲል ከነበረበት በተሻለ የመከላከል ሁኔታዎች በመኖራቸው፣ የህብረተሰቡ ግንዛቤ መሻሻል በማሳየቱ፣ የማስክና የሳኒታይዘር ምርት በሀገር ውስጥ በስፋት በመኖሩ፣ የጤና ተቋማት ዝግጁነት እና ግብአት አቅርቦት መሻሻሉ፣ የምርመራ ኪት ማምረትን ጨምሮ የላቦራቶሪ አቅንም ማገድና የዘርፈ ብዙ ምላሽ በተሻለ ሁኔታ የሚገኝ መሆኑ እንዲሁም የሀራት የምርጫ ተሞክሮን በማየት የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎቸን አማልቶ ሀገራዊ ሁኔታን ማካሄድ ይቻላል።

• ከዚህ በፊት ከነበረው የምርጫ ሂደት በተለየ መልኩ ኮቪድ 19ኝ መከላከልን ከግምት ውስጥ ያስገባ የምርጫ ስነ ምግባር ደንብ እና ማስፈጸሚያ ነነሪያዎችን ማዘጋጀትና በተዘጋጁ ዝርዝሮች መሰረት በሁሉም ደረጃ በበቂ ዝግጅቶች ወደ ትግበራ መግባት ያስፈልጋል።

• በዚህ ሂደት ውስጥ አንድ አንድ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የወረርሽኝ ስርጭት ከተከሰተ በተለየ ሁኔታ መታየት ሊያስፈልገው እንደሚችል ታሳቢ በማድረግ መዘጋጀት ያስፈልጋል ሲል ሚኒስቴሩ ምክረ ሀሳቡን አቅርቧል።

በቀረበው ሪፖርትና እና መክረ ሀሳብ ላይ የምክር ቤቱ አባላት አስተያየት እየሰጡ ሲሆን፥ ከተወያዩብ በኋላ ውሳኔ ያሳልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።ዜናው ከኤፍቢሲ አግኝተንዋል፡፡

አዉሎ ሚዲያ መስከረም 08/2013 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ