ፕሬዝዳንት ሉካሼንኮ ወደ ሞስኮ በመሄድ የጸጥታ አስከባሪ ፖሊሶች ድጋፍ ከሩሲያ እንደሚጠይቁ ተነገረ

0
114

ከሩሲያ የቤላሩስ ዋና ከተማ ሚንስክ ትናንትና እሑድ በከፍተኛ ተቃውሞ ስትናጥ ነበር የዋለችው፡፡

በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎቿ አደባባይ ነው የዋሉት፡፡

ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ደግሞ ምስጢራዊ ደኅንነቶቻቸውን አሰማርተው ሰልፈኞችን እያሳፈኑ ከባድ የሥራ ቀን አሳልፈዋል፡፡

አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ሥልጣን አልጠገብኩም እያሉ ያሉት ከ26 ዓመታት በኋላ ነው፡፡

በዘመናዊ ታሪክ በአውሮፓ ምድር እንደ ሉካሼንኮ ለረዥም ዘመን በሥልጣን መንበሩ የተቀመጠ መሪ የለም፡፡

ሉካሼንኮ አሁን ቭላድሚር ፑትንን ለማግኘት ቀጠሮ ይዘዋል፡፡ ይህ ዜና ሲጠናቀር ወደ ክሬምሊን በጉዞ ላይ ናቸው፡፡

በቤላሩስ አመጽ ከተቀሰቀሰ ወዲህ ቪላድሚር ፑቲን ከሉካሼንኮ ጋር በአካል ሲገናኙ ለመጀመርያ ጊዜ ነው የሚሆነው፡፡ዘገባው የቢቢሲ ነው።

አዉሎ ሚዲያ መስከረም 04/2013 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ