የቢቢሲ ኮምላ ዱሞር ሽልማት አሸናፊዋ !

0
131

ኬንያዊቷ የ2020 የቢቢሲ ኮምላ ዱሞር ሽልማትን አሸነፈች ። ኬንያዊቷ የምርመራ ዘጋቢና የዜና አንባቢ ቪክቶሪያ ሩባዲሪ የቢቢሲ ወርልድ ኒውስ የ 2020 ኩምላ ዱሞር ሽልማት አሸናፊ ሆናለች።ቪክቶሪያ ሩባዲሪ በኬንያ ታዋቂ በሆነው ‘ሲቲዚንስ ቴሌቪሽን ‘ዜና አቅራቢ ስትሆን በጣቢያው አበይት በሆኑ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተፅዕና ፈጣሪ የሆኑ ግለሰቦችን፣ፖለቲከኞኝ ቃለ ምልልስ በማድረግ ዝናን ያተረፈች ጋዜጠኛ ነች።

ይህ ቢቢሲ በየአመቱ የሚያዘጋጀው የሽልማት ስነስርዓት እአአ ጥር 2014 በ41 ዓመቱ በድንገት ህይወቱ ያለፈውን ዝነኛውን ጋናዊ የቢቢሲ ጋዜጠኛ ኮምላ ዱሞርን ለመዘከር ነው።ከአፍሪካ አህጉር አዲስ የሚወጡ ባለሙያዎችን ለማፍራት ለአለም ለማስተዋወቅ የሚል አላማ ባነገበው ሽልማት ለመሳተፍ አፍሪካውያን ጋዜጠኞች እንዲመዘገቡ ማስታወቂያው ወጥቶ እንደነበር ይታወሳል።ኬንያዊቷ ቪክቶሪያ ሩባዲሪ ሽልማቱ ከተጀመረ ወዲህ ስድስተኛዋ አሸናፊ እና ሁለተኛዋ ኬንያዊት መሆን ችላለች።

ኬንያዊው ዋይሂጋ ምዋራ በ2015 የተዘጋጀው የመጀመሪያውን ሽልማት አሸንፎ ነበር።ዩጋንዳዊቷ ናንሲ ካቹንጊራ፤በተከታዮቹ ሁለት ዓመታት ደግሞ ናይጄሪያውያኑ ዲዲ አኪንዬሉሬ እና አሚና ዩጉዳ አሸናፊ ሆነዋል።ቪክቶሪያ ዱባዲሪ የሽልማቱ አሸናፊ መሆኗን ተከትሎ ለንደን በሚገኘው የቢቢሲ ዋና መስሪያ ቤት ለሦስት ወራት በመቆት ልምድና ክህሎትን የምታገኝ ይሆናል።”ኮምላ ዘርፈ በዙ ስራዎች ላይ መሳተፍ የሚችል ርህሩህ እና አነቃቂ እና የተዋጣለት ጋዜጠኛ ነበር ያለች ሲሆን እኔም በጋዜጠኝነት ስራዬ የእሱን በጎ ስም ማስቀጠል እፈልጋለሁ።” ብላለች ቪክቶሪያ።

ቪክቶሪያ አያይዛም እውነታዎችን በተሟላ ሁኔታ ለተመልካች የመስጠት ችሎታው በጣም የምደነቅበት እና እሱን ለመምሰል የፈለግኩበት ክህሎት ነበር” ነው ያለችው።በቢቢሲ ዎርልድ ሰርቪስ ተገኝቼ ከተመልካች ጋር በአከባቢ፣በክልል እና በዓለም አቀፍ ደረጃ መገናኘት መቻል አዳዲስ ክህሎቶችን መማር የሚያስሚያስችል በመሆኑ አስደስቶኛል ብላለች።የቢቢሲ ወርልድ ሰርቪስ ዋና ዳይሬክተር ጄሚ አንገስ በበኩላቸው ”ቪክቶሪያን ወደ ቢቢሲ ለማምጣት በመቻላችን ደስ ብሎናል” ብለዋል፡፡

አዉሎ ሚዲያ ነሀሴ 26/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ