በትግራይ ክልል ለሚካሄደው ክልላዊ ምርጫ ከ2.7 ሚሊዮን በላይ ሰዎች መመዝገባቸው ተነገረ

0
115

ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በተካሄደው የትግራይ መራጮች ምዝገባ 2,740,888 ሰዎች መመዝገባቸውን የትግራይ ክልል የምርጫ ኮሚሽነር አቶ ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም ገልጸዋል።
ኮሚሽነሩ እንዳሉት፤ እስካሁን ሦስት የምርጫ ክርክሮች ተካሂደዋል። የመጨረሻው ክርክር ደግሞ በቀጣዩ ሐሙስ ይከናወናል።

ምርጫውን ለማስፈጸም አስፈላጊ ግብዓቶች ወደ ምርጫ ጣቢያዎች እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ መ/ር ሙሉወርቅ ተናግረዋል። 29 ሺህ 600 የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ቅሬታ ሰሚዎች እና ታዛቢዎች እንደተዘጋጁም አክለዋል።
በተጨማሪም ምርጫውን ለመታዘብ ከውጪ የሚመጡ ሰዎች የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር በተቋቋመው ግብረ ኃይል በኩል እንደሚያልፉ ኮሚሽነሩ አስረድተዋል።

በትግራይ ክልል 2,672 የምርጫ ጣቢያዎች አለ።
ባለፈው ሳምንት መመዝገብ ያልቻሉ ሰዎች ቅዳሜ እና እሑድ እንዲመዘገቡ የተደረገ ሲሆን፤ አሁን የመራጮች ምዝገባ መጠናቀቁም ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።
የምርጫ ቅስቀሳው ደግሞ አርብ ይገባደዳል ተብሏል።


አዉሎ ሚዲያ ነሀሴ 26/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ