መንግስት ለታሰሩ ጋዜጠኞች አፋጣኝ ፍትህን እንዲሰጥ የጋዜጠኞች ማህበሩ አሳሰበ

0
94

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ማህበር ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው ለታሰሩ የአስራት ቴሌቪዥን እና የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ጋዜጠኞች መንግስት አፋጣኝ ፍትህን እንዲሰጥ አሳሰበ፡፡

ባለሙያዎቹ የተያዙበት ሁኔታ ለኮሮና ወረርሽኝ የሚያጋልጥ ከመሆኑም በላይ ቤተሰብን ጨምሮ በሌሎች አካላት የመጎብኘት መብታቸው ችግር ውስጥ እንዳለ ተረድተናል ያለው ማህበሩ የባለሙያዎቹ የመጎብኘት መብት እንዲጠበቅ እና ለወረርሽኙ በማያጋልጥ ሁኔታ እንዲያዙ አሳስቧል፡፡

በቅርቡ በወላይታ ተከስቶ ከነበረው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ የጸጥታ አካላት ዎጌታ ወደተሰኘው የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያ መግባታቸውን “ተቀባይነት የሌለው ልምምድ” ሲልም ነው ያወገዘው፡፡
ሁኔታው በየትኛውም የሚዲያ ተቋም ላይ እንዳይደገምና ተስፋ የተጣለበት የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት እንዲከበርም ጠይቋል፡፡


አዉሎ ሚዲያ ነሀሴ 26/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ