ዩኤኢ የቆየው አዋጅዋን ሻረች

0
86

ዩኤኢ ከእስራኤል ጋር የሚደረጉ ግኙነቶችን ለመከልከል በ1972 ያወጣችውን አዋጅ ሻረች የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ከእስራኤል ጋር የሚደረጉ የትኞቹንም ዓይነት ግኙነቶች ለመከልከል እኤአ በ1972 ያወጣችውን አዋጅ ሻረች፡፡

ዩኤኢ ይህን ያደረገችው ከእስራኤል ጋር አዲስ የሁለትዮሽ የግንኙነት ምዕራፍ መጀመሩን ተከትሎ ነው፡፡ከሳምንት በፊት የተደረገውን ስምምነት ተከትሎ ፕሬዝዳንት ሼህ ኸሊፋ ቢን ዛይድ አልናህያን አዋጅ ቁጥር 15/72ትን በአዋጅ ቁጥር 04/20 ሽረዋል፡፡

የአዋጁ መሻር የሃገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት በማጠናከር በምጣኔ ሃብት እና በሌሎችም ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ላይ ይበልጥ እንዲተባበሩ ለማድረግ የሚያስችል ነው እንደ ሃገሪቱ የዜና አገልግሎት (WAM) ገለጻ፡፡

ከአሁን በኋላ በዩኤኢ የሚገኙ ተቋማትና ግለሰቦች በእስራኤል ከሚገኙ ግለሰቦችና ተቋማት ጋር ግንኙነት ማድረግ፣ በጋራ መስራት የሚችሉ ይሆናል፡፡የእስራኤል ምርቶችን ወደ ዩኤኢ ማስገባት፣መነገድ፣መሸጥ መለዋወጥ ይቻላልም፡፡

አዉሎ ሚዲያ ነሀሴ 23/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ