አዲሱ የፌዴራል ፖሊስ የደንብ ልብስ ይፋ ሆነ

0
160

አዲሱን የፌዴራል ፖሊስ የደንብ ልብስ በዛሬው ዕለት ይፋ ሁኗል። የፌዴራል ፖሊስን የደንብ ልብስን በአዲስ መቀየር ያስፈለገበት ምክንያት ልብሱ ለረጅም ዓመታት አገልግሎት ላይ በመቆየቱ መሆኑን የደንብ ልብሱን ይፋ ያደረጉት የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል እንደሻው ጣሰው ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በቀድሞው የደንብ ልብስ ተጠቅመው የተለያዩ ወንጀሎች ሲፈፀሙ የነበሩ አካላት በመበራከታቸው መሆኑንም እንደምክንያት አስቀምጠዋል። በሌላ በኩል የፌዴራል ፖሊስ አባላት በአዲሱ ዓመት በአዲስ መንፈስ ወደ ሥራ እንዲገቡ የታሰበ መሆኑንም ነው የገለጹት።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ በእንግድነት የተገኙት የሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል በበኩላቸው፣ የፖሊስ የደንብ ልብስን መቀየር እንደ ሀገር የተጀመረው ሪፎርም አካል መሆኑን አስታውቀዋል። ዜናው የኢቢሲ ነው።

አዉሎ ሚዲያ ነሀሴ 23/2012 ዓ.ም

መልስ አስቀምጥ

Please enter your comment!
እባክዎ ስምዎን እዚህ ያስገቡ